La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 11:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የተ​ቀ​ላ​ቀሉ ሕዝብ እጅግ ጐመጁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተቀ​ም​ጠው እን​ዲህ እያሉ አለ​ቀሱ፥ “ሥጋ ማን ያበ​ላ​ናል?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ድብልቁ ሕዝብ ሌላ ምግብ ጐመጀ፤ እስራኤላውያንም እንዲህ እያሉ ያጕረመርሙ ጀመር፤ “ምነው የምንበላው ሥጋ ባገኘን ኖሮ!

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በእነርሱም መካከል የነበረው የተለያየ ሕዝብ እጅግ ጐመጀ፤ የእስራኤልም ልጆች ዳግመኛ ዘወር በለው አለቀሱ እንዲህም አሉ፦ “የምንበላውን ሥጋ ማን ይሰጠናል?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከእስራኤላውያን ጋር የሚጓዙ የውጪ አገር ሰዎች ሥጋ ለመብላት የነበራቸው ፍላጎት ከፍተኛ ነበር፤ እስራኤላውያንም እንዲህ እያሉ ማልቀስ ጀመሩ፦ “የምንበላውን ሥጋ ከየት እናገኛለን!

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በመካከላቸውም የነበሩ ልዩ ልዩ ሕዝብ እጅግ ጐመጁ፤ የእስራኤል ልጆች ደግሞ ያለቅሱ ነበር፦ የምንበላውን ሥጋ ማን ይሰጠናል?

Ver Capítulo



ዘኍል 11:4
16 Referencias Cruzadas  

ሕጉ​ንም በሰሙ ጊዜ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር የተ​ደ​ባ​ለ​ቀ​ውን ሕዝብ ሁሉ ለዩ።


ከጨ​ለ​ማና ከሞት ጥላ አወ​ጣ​ቸው፥ እግር ብረ​ታ​ቸ​ው​ንም ሰበረ።


ደግ​ሞም ሌላ ብዙ ድብ​ልቅ ሕዝብ፥ መን​ጎ​ችና ላሞ​ችም እጅግ ብዙም ከብ​ቶች ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወጡ።


“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማን​ጐ​ራ​ጐር ሰማሁ፦ ማታ ሥጋን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ማለ​ዳም እን​ጀ​ራን ትጠ​ግ​ባ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ በላ​ቸው።”


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አሉ​አ​ቸው፥ “በሥ​ጋው ምን​ቸት አጠ​ገብ ተቀ​ም​ጠን እስ​ክ​ን​ጠ​ግብ ድረስ እን​ጀ​ራና ሥጋ በም​ን​በ​ላ​በት ጊዜ በግ​ብፅ ምድር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ምነው በሞ​ትን! ይህን ጉባኤ ሁሉ በራብ ልት​ገ​ድሉ እኛን ወደ​ዚች ምድረ በዳ አም​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና።”


እና​ን​ተም፦ አይ​ደ​ለም፤ ሰልፍ ወደ​ማ​ና​ይ​ባት፥ የመ​ለ​ከ​ትም ድምፅ ወደ​ማ​ን​ሰ​ማ​ባት፥ እን​ጀ​ራ​ንም ወደ​ማ​ን​ራ​ብ​ባት ወደ ግብፅ ምድር እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በዚ​ያም እን​ቀ​መ​ጣ​ለን ብትሉ፥


ሕዝ​ቡ​ንም በላ​ቸው፦ ሥጋ ማን ያበ​ላ​ናል? በግ​ብፅ ደኅና ነበ​ረ​ልን እያ​ላ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አል​ቅ​ሳ​ች​ኋ​ልና ለነገ ተቀ​ደሱ፤ ሥጋ​ንም ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሥጋን ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ ትበ​ሉ​ማ​ላ​ችሁ።


ማኅ​በ​ሩም ሁሉ ድም​ፃ​ቸ​ውን አን​ስ​ተው ጮኹ፤ ሕዝ​ቡም ሌሊ​ቱን ሁሉ አለ​ቀሱ።


በግ​ብፅ ምድ​ርና በም​ድረ በዳ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ተአ​ም​ራ​ቴ​ንና ክብ​ሬን ያዩ እነ​ዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ስለ ተፈ​ታ​ተ​ኑኝ፥ ቃሌ​ንም ስላ​ል​ሰሙ፥


በም​ድረ በዳ ትገ​ድ​ለን ዘንድ፥ በእ​ኛም ላይ አለ​ቃ​ችን ትሆን ዘንድ ወተ​ትና ማር ከም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ምድር ያወ​ጣ​ኸን አነ​ሰ​ህን?


ነገር ግን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ልበ​ሱት፤ የሥ​ጋ​ች​ሁ​ንም ምኞት አታ​ስቡ።


እነ​ርሱ እንደ ተመኙ እኛ ደግሞ ክፉ እን​ዳ​ን​መኝ እነ​ርሱ ለእኛ ምሳሌ ሆኑ​ልን።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን አያ​ስ​ቱ​አ​ችሁ፤ ክፉ ነገር መል​ካም ጠባ​ይን ያበ​ላ​ሻ​ልና።


“በው​ዕ​የት፥ በፈ​ተ​ናም በም​ኞት መቃ​ብ​ርም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አስ​ቈ​ጣ​ች​ሁት።