ነህምያ 7:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፋሮስ ልጆች ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሰባ ሁለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፋሮስ ዘሮች 2,172 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፓርዖሽ ልጆች፥ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሰባ ሁለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከምርኮ ከተመለሱት ከእያንዳንዱ ጐሣ ተወጣጥተው የተመዘገቡት የእስራኤል ጐሣዎችና የትውልዳቸው ብዛት ይህ ነው፦ ከፓርዖሽ ወገን የተመዘገቡ 2172 ከሸፋጥያ ወገን የተመዘገቡ 372 ከአራሕ ወገን የተመዘገቡ 652 የኢያሱና የኢዮአብ ትውልድ ጐሣ ከሆነው ከፓሐትሞአብ ወገን የተመዘገቡ 2818 ከዔላም ወገን የተመዘገቡ 1254 ከዛቱ ወገን የተመዘገቡ 845 ከዛካይ ወገን የተመዘገቡ 760 ከቢኑይ ወገን የተመዘገቡ 648 ከቤባይ ወገን የተመዘገቡ 628 ከዓዝጋድ ወገን የተመዘገቡ 2322 ከአዶኒቃም ወገን የተመዘገቡ 667 ከቢግዋይ ወገን የተመዘገቡ 2067 ከዓዲን ወገን የተመዘገቡ 655 ሕዝቅያስ ተብሎ ከሚጠራው ከአጤር ወገን የተመዘገቡ 98 ከሐሹም ወገን የተመዘገቡ 328 ከቤጻይ ወገን የተመዘገቡ 324 ከሐሪፍ ወገን የተመዘገቡ 112 ከገባዖን ወገን የተመዘገቡ 95 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቁጥር ይህ ነው፥ የፋሮስ ልጆች፥ ሁለት ሺህ መቶ ሰባ ሁለት። |
ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከአዛርያስ፥ ከረዓምያ፥ ከሄሜኔስ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበልሰማ፥ ከሚስፌሬት፥ ከዕዝራ፥ ከበጉዋይ፥ ከነሑም፥ ከበዓና፥ ከመስፈር ጋር መጡ። ከእስራኤልም ሕዝብ የወንዶች ቍጥር ይህ ነው፥