La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ነህምያ 7:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንና ሹሞ​ቹን፥ ሕዝ​ቡ​ንም ሰብ​ስቤ በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው እቈ​ጥ​ራ​ቸው ዘንድ ልቤን አነ​ሣሣ፤ አስ​ቀ​ድ​መው የመ​ጡ​ት​ንም ሰዎች የት​ው​ልድ መጽ​ሐ​ፋ​ቸ​ውን አገ​ኘሁ፤ በእ​ር​ሱም እን​ደ​ዚህ ተጽፎ አገ​ኘሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ መኳንንቱን፣ ሹማምቱንና ተራውን ሕዝብ ሰብስቤ በየቤተ ሰቡ ይመዘገቡ ዘንድ እግዚአብሔር ይህን በልቤ አኖረ። ወደ ምድራቸው ለመመለስ የመጀመሪያ የሆኑትን ሰዎች የትውልድ ሐረግ መዝገብ አገኘሁ፤ ተጽፎ ያገኘሁትም ይህ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አምላኬም መኳንንቱን፥ ሹማምቱንና ሕዝቡን ሰብስቤ እንድቆጥራቸው በልቤ አስቀመጠ፤ አስቀድመው የመጡትን ሰዎች የትውልድ መጽሐፋቸውን አገኘሁ፥ በእርሱም እንደዚህ ተጽፎ አገኘሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔርም ሕዝቡንና መሪዎቻቸው የሆኑ ባለሥልጣኖችን እንድሰበስብና የቤተሰባቸውን የትውልድ ሐረግ አመዘጋገብ እንድቈጣጠር አነሣሣኝ፤ ቀደም ባለው ጊዜ የተመለሱትንም ምርኮኞች የትውልድ ሐረግ ማስረጃ መዝገብ አገኘሁ፤ ያገኘሁትም ማስረጃ ከዚህ የሚከተለው ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አምላኬም ታላቆቹንና ሹማምቱን ሕዝቡንም ሰብስቤ እቈጥራቸው ዘንድ በልቤ አደረገ፥ አስቀድመው የመጡትን ሰዎች የትውልድ መጽሐፋቸውን አገኘሁ፥ በእርሱም እንደዚህ ተጽፎ አገኘሁ።

Ver Capítulo



ነህምያ 7:5
15 Referencias Cruzadas  

እነ​ዚህ በት​ው​ልድ መጽ​ሐፍ ትው​ል​ዳ​ቸ​ውን ፈለጉ፤ ነገር ግን አል​ተ​ገ​ኘም፤ ከክ​ህ​ነ​ትም ተከ​ለ​ከሉ።


ያባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ያከ​ብር ዘንድ ይህን ነገር በን​ጉሡ ልብ ያኖረ፥


አም​ላኬ ሆይ፥ ለዚህ ሕዝብ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ሁሉ ለበ​ጎ​ነት አስ​ብ​ልኝ።


አም​ላኬ ሆይ፥ ስለ​ዚህ ሥራ​ቸው ጦቢ​ያ​ንና ሰን​ባ​ላ​ጥን፥ ነቢ​ይ​ቱ​ንም ኖዓ​ድ​ያን ያስ​ፈ​ራ​ሩኝ ዘንድ የፈ​ለ​ጉ​ትን፥ የቀ​ሩ​ት​ንም ነቢ​ያት አስብ።


ከተ​ማ​ዪ​ቱም ሰፊና ታላቅ ነበ​ረች፤ በው​ስ​ጥዋ የነ​በሩ ሕዝብ ግን ጥቂ​ቶች ነበሩ፤ ቤቶ​ቹም ገና አል​ተ​ሠ​ሩም ነበር።


እነ​ዚህ በት​ው​ልድ መጽ​ሐፍ ትው​ል​ዳ​ቸ​ውን ፈለጉ፤ ነገር ግን አል​ተ​ገ​ኘም፤ ከክ​ህ​ነ​ትም ተከ​ለ​ከሉ።


እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከፊቱም ዕውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፤


በመንገድህ ሁሉ ጥበብን ዕወቃት፥ እርስዋም መንገድህን ታቃናልሃለች።


ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አሁን እኔ ባለ​ሁ​በት አለሁ፤ ለእ​ኔም የሰ​ጠኝ ጸጋው ለከ​ንቱ የሆ​ነ​ብኝ አይ​ደ​ለም፤ እኔም ከሁሉ ይልቅ ደከ​ምሁ፤ ነገር ግን በእኔ ላይ ያደ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አጸ​ናኝ እንጂ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም።


ኀይ​ላ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ሆነ ከእኛ ከራ​ሳ​ችን እንደ ሆነ አድ​ር​ገን ምንም ልና​ስብ አይ​ገ​ባ​ንም።


በቲቶ ልብ ስለ እና​ንተ ያን መት​ጋት የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ነው።


በኀ​ይሉ እን​ደ​ሚ​ረ​ዳኝ እንደ ረድ​ኤቱ መጠን ስለ እርሱ እደ​ክ​ማ​ለሁ፤ እጋ​ደ​ላ​ለ​ሁም።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! አትሳቱ።