La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ነህምያ 4:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም እንደ ዐወ​ቅ​ን​ባ​ቸው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምክ​ራ​ቸ​ውን ከንቱ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሰሙ፤ እኛም ሁላ​ችን ወደ ቅጥሩ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችን ወደ ሥራ​ችን ተመ​ለ​ስን።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አድማቸውን እንዳወቅንባቸውና እግዚአብሔርም ዕቅዳቸውን ከንቱ እንዳደረገባቸው ጠላቶቻችን በሰሙ ጊዜ፣ ሁላችን ወደ ቅጥሩ፣ እያንዳንዳችንም ወደየሥራችን ተመለስን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኛ ሥራውን ሠራን፤ እኩሌቶቹ ደግሞ ጎሕ ሲቀድ ጀምሮ ከዋክብት እስኪወጡ ድረስ ጦር ይይዙ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጠላቶቻችንም የተማማሉበትን አድማ የደረስንበት መሆኑን ሰሙ፤ እግዚአብሔርም ዕቅዳቸውን እንዳከሸፈባቸው ተገነዘቡ፤ ከዚያ በኋላ ሁላችንም የቅጽሩን ግንብ መሥራታችንን ቀጠልን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጠላቶቻችንም ይህ ነገር እንደ ደረሰልን፥ እግዚአብሔርም ምክራቸውን ከንቱ እንዳደረገው ሰሙ፥ እኛም ሁላችን ወደ ቅጥሩ እያንዳንዳችን ወደ ሥራችን ተመለስን።

Ver Capítulo



ነህምያ 4:15
13 Referencias Cruzadas  

አኪ​ጦ​ፌል ከአ​ቤ​ሴ​ሎም ጋር በሴራ አንድ ነው ብለው ለዳ​ዊት ነገ​ሩት፤ ዳዊ​ትም፥ “አቤቱ የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልን ምክር ለውጥ” አለ።


አቤ​ሴ​ሎ​ምና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ “የአ​ር​ካ​ዊው የኩሲ ምክር ከአ​ኪ​ጢ​ፌል ምክር ይሻ​ላል” አሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ቤ​ሴ​ሎም ላይ ክፉ ያመጣ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካ​ሚ​ቱን የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልን ምክር እን​ዲ​በ​ትን አዘዘ።


ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ እኩ​ሌ​ቶቹ ብላ​ቴ​ኖች ሥራ ይሠሩ ነበር፤ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም ጋሻና ጦር፥ ቀስ​ትና ጥሩ​ርም ይዘው በፊ​ትና በኋላ ይጠ​ብቁ ነበር፤ አለ​ቆ​ቹም ከይ​ሁዳ ቤት ሁሉ በኋላ ይቆሙ ነበር።


ጥበብና ብርታት፥ ምክርም፥ በኃጥእ ዘንድ የሉም።


በሟ​ርት ሙት እና​ስ​ነ​ሣ​ለን የሚ​ሉ​ትን፥ ከል​ባ​ቸ​ውም አን​ቅ​ተው ሐሰት የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን ሰዎች ምል​ክት የሚ​ለ​ውጥ ማን ነው? ጥበ​በ​ኞ​ቹ​ንም ወደ ኋላ ይመ​ል​ሳል፤ ምክ​ራ​ቸ​ው​ንም ስን​ፍና ያደ​ር​ጋል።


ምክ​ርን ብት​መ​ክ​ሩም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክ​ራ​ች​ሁን ይለ​ው​ጣል፤ የተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁ​ትም ነገር አይ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር ነውና።


ቤቱን ትቶ ወደ ሌላ አገር እንደ ሄደ ሰው ነው፤ ለባሮቹም ሥልጣን ለእያንዳንዱም ሥራውን ሰጥቶ በረኛውን እንዲተጋ አዘዘ።


ለሥራ ከመ​ት​ጋት አት​ስ​ነፉ፤ በመ​ን​ፈስ ሕያ​ዋን ሁኑ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ፤