“ዓለምን ሁሉ የምትገዛ፥ የአባቶቻችን የአብርሃምና የይስሐቅ፥ የያዕቆብም የጻድቃን ልጆቻቸውም አምላክ ሆይ፥ ሰማይንና ምድርን ከዓለሞቻቸው ጋር የፈጠርህ፥
ነህምያ 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአስናሃ ልጆችም የዓሣ በር ሠሩ፤ ሠረገሎቹንም አኖሩ፤ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቍልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዓሣ በሩን የሃስናአ ልጆች ሠሩ፤ እነርሱም ምሰሶዎቹን አቁመው መዝጊያዎቹን፣ መቀርቀሪያዎቹንና መወርወሪያዎቹን በየቦታቸው አኖሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የስናአ ልጆች “የዓሣ በር” ሠሩ፤ ሰረገሎቹን አኖሩ፥ በሮቹን አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም ሠሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሃስናአ ጐሣ አባሎች የዓሣ ቅጽር በር የተባለውን ሠሩ፤ ምሰሶዎችንም አቆሙለት፤ በሮችንም ገጠሙ፤ ለበሮቹም መዝጊያ፥ መወርወሪያና ቊልፎችን አበጁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሃስናአ ልጆችም የዓሣ በር ሠሩ፥ ሰረገሎቹን አኖሩ፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ። |
“ዓለምን ሁሉ የምትገዛ፥ የአባቶቻችን የአብርሃምና የይስሐቅ፥ የያዕቆብም የጻድቃን ልጆቻቸውም አምላክ ሆይ፥ ሰማይንና ምድርን ከዓለሞቻቸው ጋር የፈጠርህ፥
ከኤፍሬምም በር በላይ፥ በአሮጌው በርና በዓሣ በር፥ በአናንኤልም ግንብ፥ በሃሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፤ በዘበኞችም በር አጠገብ ቆሙ።
በቤቱም አጠገብ ላለው ለግንብ በሮች፥ ለከተማውም ቅጥር፥ ለምገባበትም ቤት እንጨት እንዲሰጠኝ ለንጉሡ ዱር ጠባቂ ለአሳፍ ደብዳቤ ይሰጠኝ” አልሁት። ንጉሡም ሁሉን ሰጠኝ። የከበረች የአምላኬ እጅ ከእኔ ጋር ነበረችና።
በአጠገባቸውም የቆስ ልጅ የኡርያ ልጅ ሚራሞት ይሠራ ጀመረ። በአጠገባቸውም የሜሴዜቤል ልጅ የበራክያ ልጅ ሜሱላም ይሠራ ጀመረ። በአጠገባቸውም የበሃና ልጅ ሳዶቅ ይሠራ ጀመረ።
የፋሴሓ ልጅ ኢዮዳሄና የበሶድያ ልጅ ሜሱላም አሮጌውን በር አደሱ፤ ሰረገሎቹን አኖሩ፤ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፤ ቍልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ።
እንዲህም ሆነ፤ ቅጥሩን እንደ ሠራሁ፥ ከፍራሹም አንዳች እንዳልቀረበት ሰንባላጥና ጦቢያ ዓረባዊውም ጌሳም የቀሩትም ጠላቶቻችን ሰሙ፤ ነገር ግን እስከዚያ ጊዜ ድረስ በበሮቹ ውስጥ ሳንቃዎቹን አላቆምሁም ነበር።