ነህምያ 3:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ናታኒምም በዖፌል በውኃው በር አንጻር በምሥራቅ በኩል ወጥቶ በቆመው ግንብ አጠገብ እስካለው ስፍራ ድረስ ተቀመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዖፌል ኰረብታ ላይ የሚኖሩት የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች የውሃ በር ተብሎ ከሚጠራው ትይዩ ጀምሮ በስተምሥራቅ እስከሚገኘው ግንብ ድረስ መልሰው ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዖፌል የተቀመጡ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች በምሥራቅ በኩል ካለው ከ “የውኃ በር” ፊት ለፊት ጀምሮ እስከ “የወጣው ግንብ” ድረስ አደሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናታኒምም በዖፌል በውኃው በር አንጻር በምሥራቅ በኩል ወጥቶ ባቆመው ግንብ አጠገብ እስካለው ስፍራ ድረስ ተቀመጡ። |
“ዓለምን ሁሉ የምትገዛ፥ የአባቶቻችን የአብርሃምና የይስሐቅ፥ የያዕቆብም የጻድቃን ልጆቻቸውም አምላክ ሆይ፥ ሰማይንና ምድርን ከዓለሞቻቸው ጋር የፈጠርህ፥
የቀሩትም ሕዝብ፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ በረኞቹም፥ መዘምራንም፥ ናታኒምም፥ ከምድርም አሕዛብ ራሳቸውን የለዩና ወደ እግዚአብሔር ሕግ የገቡ ሁሉ፥ ሚስቶቻቸውም፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም፥ የሚያውቁትና የሚያስተውሉትም ሁሉ ወንድሞቻቸውንና ታላላቆቻቸውን አበረታቱ፤
በምንጭም በር አቅንተው ሄዱ፤ በዳዊትም ከተማ ደረጃ፥ በቅጥሩም መውጫ፥ ከዳዊትም ቤት በላይ እስከ ውኃው በር ድረስ በምሥራቅ በኩል ሄዱ።
ሰባተኛውም ወር በደረሰ ጊዜ የእስራኤል ልጆች በከተሞቻቸው ነበሩ። ሕዝቡም ሁሉ በውኃው በር ፊት ወዳለው አደባባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ፤ እግዚአብሔርም ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴን ሕግ መጽሐፍ ያመጣ ዘንድ ጸሓፊውን ዕዝራን ነገሩት።
ሕዝቡም ወጥተው አመጡ፤ እያንዳንዱም በቤቱ ሰገነት ላይ፥ በአደባባዩም ላይ፥ በእግዚአብሔርም ቤት አደባባይ ላይ፥ በውኃውም በር አደባባይና በኤፍሬም በር አደባባይ ላይ ዳስ ሠሩ።
በውኃውም በር ፊት ባለው አደባባይ ላይ ቆሞ፥ በወንዶችና በሴቶች በሚያስተውሉትም ፊት፥ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ቀትር ድረስ አነበበው፤ የሕዝቡም ሁሉ ጆሮ የሕጉን መጽሐፍ ለመስማት ያደምጥ ነበር።
የበለጸገች ከተማና ቤቶችዋ ምድረ በዳ ይሆናሉ። የከተማውን ሀብትና ያማሩ ቤቶችን ይተዋሉ፤ አንባዎችም ለዘለዓለም ዋሻ፥ የምድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመንጎችም ማሰማሪያ ይሆናሉ።