Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 27:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት የላ​ይ​ኛ​ውን በር ሠራ፤ በዖ​ፌ​ልም ቅጥር ላይ ብዙ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ኢዮአታም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የላይኛውን በር ሠራ፤ በዖፌልም በኩል ባለው ቅጥር ላይ፣ አያሌ የማሻሻል ተግባር አከናወነ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የጌታን ቤት የላይኛውን በር ሠራ፥ በዖፌልም ቅጥር ላይ መጠነ ሰፊ ግንብ ገነባ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ኢዮአታም የቤተ መቅደሱን ሰሜናዊ በር እንደገና ሠራ፤ በተጨማሪም በኢየሩሳሌም በሚገኘው ዖፌል ተብሎ በሚጠራው ኰረብታማ ቦታ የከተማ ቅጽሮችን በመሥራት ብዙ ሥራ አከናውኖአል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የእግዚአብሔርን ቤት የላይኛውን በር ሠራ፤ በዖፌልም ቅጥር ላይ እጅግ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 27:3
6 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን የጣ​ዖ​ታ​ቱን ቤት አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም ገና በኮ​ረ​ብ​ቶች ላይ ይሠ​ዉና ያጥኑ ነበር። እር​ሱም የላ​ይ​ኛ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት በር ሠራ።


የመቶ አለ​ቆ​ች​ንም፥ ከበ​ር​ቴ​ዎ​ች​ንም፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም አለ​ቆች፥ የሀ​ገ​ሩ​ንም ሕዝብ ሁሉ ወሰደ፤ ንጉ​ሡ​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አወ​ረ​ዱት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በው​ስ​ጠ​ኛው በር በኩል ወደ ንጉሡ ቤት አመ​ጡት፤ ንጉ​ሡ​ንም በመ​ን​ግ​ሥቱ ዙፋን ላይ አስ​ቀ​መ​ጡት።


“ዓለ​ምን ሁሉ የም​ት​ገዛ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐቅ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም የጻ​ድ​ቃን ልጆ​ቻ​ቸ​ውም አም​ላክ ሆይ፥ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ከዓ​ለ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር የፈ​ጠ​ርህ፥


ጳስ​ኮ​ርም ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን ገረ​ፈው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በነ​በ​ረው በላ​ይ​ኛው በብ​ን​ያም በር ባለው አዘ​ቅት ውስጥ ጣለው።


የይ​ሁ​ዳም አለ​ቆች ይህን በሰሙ ጊዜ ከን​ጉሡ ቤት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወጡ፤ በአ​ዲ​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ደጅ መግ​ቢያ ተቀ​መጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos