ወደ እግዚአብሔርም ይመልሱአቸው ዘንድ ነቢያትን ይሰድድላቸው ነበር፤ መሰከሩባቸውም፤ እነርሱ ግን አላደመጡም።
ነህምያ 13:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ወራት በይሁዳ በሰንበት ቀን የወይን መጭመቂያን የሚረግጡትን፥ ነዶም የሚከምሩትን፥ የወይኑን ጠጅና የወይኑን ዘለላ፤ በለሱንም፥ ልዩ ልዩም ዓይነት ሸክም በአህዮች ላይ የሚጭኑትን፥ በሰንበትም ቀን ወደ ኢየሩሳሌም የሚያስገቡትን አየሁ፤ ገበያም ባደረጉበት ቀን አስመሰከርሁባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእነዚያ ቀናት በይሁዳ በሰንበት ቀን የወይን መጭመቂያ የሚረግጡ፣ እህል የሚያስገቡና፣ የወይን ጠጅ፣ የወይን ዘለላ፣ የበለስና ሌሎችን የጭነት ዐይነቶች ሁሉ በአህያ ላይ የሚጭኑ ሰዎች አየሁ፤ ይህን ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ያስገቡ የነበረው በሰንበት ቀን ነበረ። ስለዚህ በዚያ ቀን ምግብ እንዳይሸጡ ከለከልኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ወራት በይሁዳ በሰንበት ቀን የወይን መጥመቂያን የሚረግጡትን፥ ነዶም የሚከመሩትን፥ የወይኑን ጠጅና የወይኑን ዘለላ በለሱንም ልዩ ልዩም ዓይነት ሸክም በአህዮች ላይ የሚጭኑትን፥ በሰንበትም ቀን ወደ ኢየሩሳሌም የሚያስገቡትን አየሁ፥ ገበያ ባደረጉበትም ቀን አስመሰከርሁባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእነዚያም ቀኖች በይሁዳ በሰንበት ቀን ወይን የሚጨምቁ፥ እህልን፥ ወይን ጠጅን፥ የወይን ዘለላን፥ በለስን፥ ሌሎችንም ነገሮች ሁሉ በአህያ የሚጭኑ መሆናቸውን አየሁ፤ እነዚህንም ሁሉ በሰንበት ቀን ወደ ኢየሩሳሌም አምጥተው እንዳይሸጡ አስጠነቀቅኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ወራት በይሁዳ በሰንበት ቀን የወይን መጥመቂያን የሚረግጡትን፥ ነዶም የሚከመሩትን፥ የወይኑን ጠጅና የወይኑን ዘለላ በለሱንም ልዩ ልዩም ዓይነት ሸክም በአህዮች ላይ የሚጭኑትን፥ በሰንበትም ቀን ወደ ኢየሩሳሌም የሚያስገቡትን አየሁ፥ ገበያ ባደረጉበትም ቀን አስመሰከርሁባቸው። |
ወደ እግዚአብሔርም ይመልሱአቸው ዘንድ ነቢያትን ይሰድድላቸው ነበር፤ መሰከሩባቸውም፤ እነርሱ ግን አላደመጡም።
የምድርንም አሕዛብ ሸቀጥና ልዩ ልዩ እህል ሊገበዩ በሰንበት ቀን ቢያመጡ በሰንበት ወይም በተቀደሰው ቀን ከእነርሱ አንገዛም፤ ሰባተኛውንም ዓመት እናከብራለን፤ ከሰውም ዕዳ ማስከፈልን እንተዋለን።
ደግሞም በእርስዋ የተቀመጡ ነበሩ፤ እነርሱም ዓሣዎችን፥ ልዩ ልዩም ዓይነት ሸቀጥ አምጥተው በሰንበት ቀን በኢየሩሳሌም ለይሁዳ ልጆች ይሸጡ ነበር።
እኔም አስመሰከርሁባቸውና፥ “ከቅጥሩ ውጭ ለምን ታድራላችሁ? እንደ ገና ብታደርጉት እጆችን አነሣባችኋለሁ” አልኋቸው። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ በሰንበት ቀን እንደ ገና አልመጡም።
ወደ ሕግህም ትመልሳቸው ዘንድ አስመሰከርህባቸው፤ ነገር ግን አልሰሙህም፤ ሰውም ባደረገው ጊዜ በሕይወት የሚኖርበትን ትእዛዝህንና ፍርድህን ተላለፉ፤ ጀርባቸውን ሰጡ፤ አንገታቸውንም አደነደኑ፤ አልሰሙምም።
“ስድስት ቀን ሥራህን ትሠራለህ፤ በሰባተኛውም ቀን ታርፋለህ። በምትዘራበትና በምታጭድበት ዘመን ታርፋለህ።
ስድስት ቀን ሥራህን ትሠራለህ፤ በሰባተኛው ቀን ታርፋለህ፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ሰንበት ነው፤ የሚሠራበትም ሁሉ ይሙት።
ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ፥ ሰንበትንም ደስታ፥ ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ብታደርገው፥ ክፉ ሥራን ለመሥራት እግርህን ባታነሣ፥ በአፍህም ክፉ ነገርን ባትናገር፥
እኔን ፈጽሞ ብትሰሙ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በሰንበትም ቀን በዚህች ከተማ በሮች ሸክም ባታገቡ፥ የሰንበትንም ቀን ብትቀድሱ፥ ሥራንም ሁሉ ባትሠሩባት፥
ነገር ግን የሰንበትን ቀን እንድትቀድሱ፥ በሰንበትም ቀን ሸክምን ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች እንዳትገቡ የነገርኋችሁን ባትሰሙኝ፥ በበሮችዋ ላይ እሳትን አነድዳለሁ፤ የኢየሩሳሌምንም ግንቦች ትበላለች፤ አትጠፋምም።
እናንተ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ! እግዚአብሔር፦ ወደ ግብፅ አትግቡ ብሎ ተናግሮባችኋልና ዛሬ እንዳስጠነቀቅኋችሁ በእርግጥ ዕወቁ።
ነገር ግን የእስራኤልን ቤት በምድረ በዳ በትእዛዜ ሂዱ አልኋቸው፤ አልሄዱምም፤ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርበትንም ሕጌን አፈረሱ፤ ሰንበታቴንም ፈጽመው አረከሱ። በዚህም ጊዜ አጠፋቸው ዘንድ ቍጣዬን በምድረ በዳ አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።
“እህልን እንሸጥ ዘንድ መባቻው መቼ ያልፋል? የኢፍ መስፈሪያውንም እያሳነስን፥ ሰቅሉንም እያበዛን፥ በሐሰተኛም ሚዛን እያታለልን፥
ወደ እግዚአብሔር መመለስንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንን ለአይሁድና ለአረማውያን እየመሰከርሁ፤
እንግዲህ በልባቸው ከንቱ አሳብ እንደሚኖሩ እንደ አሕዛብ እንዳትኖሩ ይህን እላለሁ፤ በእግዚአብሔርም እመሰክራለሁ።
አምላክህንም እግዚአብሔርን ፈጽሞ ብትረሳ፥ ሌሎችንም አማልክት ብትከተል፥ ብታመልካቸውም፥ ብትሰግድላቸውም፥ ፈጽሞ እንደምትጠፋ እኔ ዛሬውኑ ሰማይንና ምድርን አስመሰክርብሃለሁ።
አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።