Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ገላትያ 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ደግ​ሞም ለተ​ገ​ዘረ ሰው ሁሉ የኦ​ሪ​ትን ሕግ መፈ​ጸም እን​ደ​ሚ​ገ​ባው እመ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 መገረዝ ለሚፈልግ ሁሉ ሕግን በሙሉ የመፈጸም ግዴታ እንዳለበት እንደ ገና ለእያንዳንዱ በግልጽ እናገራለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የተገረዘ ሰው ሁሉ ሕግን በሙሉ የመፈጸም ግዴታ አለበት ብዬ ደግሜ እመሰክራለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 “መገረዝ ያስፈልገኛል” ብሎ የሚገረዝ ሁሉ “ሕግን በሙሉ የመፈጸም ግዴታ አለበት” ብዬ እንደገና አስጠነቅቀዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሕግንም ሁሉ እንዲፈጽም ግድ አለበት ብዬ ለሚገረዙት ሁሉ ለእያንዳንዶች ደግሜ እመሰክራለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ገላትያ 5:3
19 Referencias Cruzadas  

በኦ​ሪት ሕግ ያሉ ሁሉ በእ​ር​ግ​ማን ውስጥ ይኖ​ራሉ፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በዚህ በኦ​ሪት መጽ​ሐፍ ውስጥ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ የማ​ይ​ፈ​ጽ​ምና የማ​ይ​ጠ​ብቅ ርጉም ይሁን።”


ኦሪ​ት​ንም ብት​ፈ​ጽም ግዝ​ረት ትጠ​ቅ​ም​ሃ​ለች፤ ኦሪ​ትን ባት​ፈ​ጽም ግን ግዝ​ረ​ትህ አለ​መ​ገ​ዘር ትሆ​ን​ብ​ሃ​ለች።


“የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ያደ​ርግ ዘንድ የማ​ያ​ጸና ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።


እን​ግ​ዲህ በል​ባ​ቸው ከንቱ አሳብ እን​ደ​ሚ​ኖሩ እንደ አሕ​ዛብ እን​ዳ​ት​ኖሩ ይህን እላ​ለሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እመ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ።


ዛሬ ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው ምድር ገና ሳላ​ገ​ባ​ቸው ክፋ​ታ​ቸ​ውን አው​ቃ​ለ​ሁና፥ ከአ​ፋ​ቸ​ውና ከል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም አፍ አት​ረ​ሳ​ምና ብዙ ክፉ ነገ​ርና ጭን​ቀት በደ​ረ​ሰ​ባ​ቸው ጊዜ ይህች መዝ​ሙር ምስ​ክር ሆና በፊ​ታ​ቸው ትቆ​ማ​ለች።”


አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሞ ብት​ረሳ፥ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት ብት​ከ​ተል፥ ብታ​መ​ል​ካ​ቸ​ውም፥ ብት​ሰ​ግ​ድ​ላ​ቸ​ውም፥ ፈጽሞ እን​ደ​ም​ት​ጠፋ እኔ ዛሬ​ውኑ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን አስ​መ​ሰ​ክ​ር​ብ​ሃ​ለሁ።


ደግማችሁም ‘ማንም በመሠዊያው የሚምል ምንም የለበትም፤ ማንም በላዩ ባለው መባ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል፤’ ትላላችሁ።


እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን።


አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መመ​ለ​ስ​ንና በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ማመ​ንን ለአ​ይ​ሁ​ድና ለአ​ረ​ማ​ው​ያን እየ​መ​ሰ​ከ​ርሁ፤


ሌላም ብዙ ነገር ነገ​ራ​ቸው፤ “ከዚህ ከክፉ ዓለ​ምም ነፍ​ሳ​ች​ሁን አድኑ” ብሎ መከ​ራ​ቸው።


አም​ስት ወን​ድ​ሞች ስለ አሉኝ ይን​ገ​ራ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ደግሞ ወደ​ዚች የሥ​ቃይ ቦታ እን​ዳ​ይ​መጡ ይስሙ።’


“እናንተ ‘ማንም በቤተ መቅደስ የሚምል ምንም የለበትም፤ ማንም በቤተ መቅደስ ወርቅ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል፤’ የምትሉ፥ ዕውሮች መሪዎች፥ ወዮላችሁ።


ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ችን፥ አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሕግ​ህን አል​ጠ​በ​ቁም፤ ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንና የመ​ሰ​ከ​ር​ህ​ባ​ቸ​ውን ምስ​ክ​ር​ህ​ንም አል​ሰ​ሙም።


ከይ​ሁዳ ሀገ​ርም የወ​ረዱ ሰዎች፥ “እንደ ሙሴ ሕግ ካል​ተ​ገ​ዘ​ራ​ችሁ ልት​ድኑ አት​ች​ሉም” እያሉ ወን​ድ​ሞ​ችን ያስ​ተ​ምሩ ነበር።


እነሆ፥ እኔ ጳው​ሎስ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ “ብት​ገ​ዘ​ሩም በክ​ር​ስ​ቶስ ዘንድ ምንም አይ​ጠ​ቅ​ማ​ች​ሁም።”


በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ በፍ​ቅር የም​ት​ሠራ እም​ነት እንጂ መገ​ዘር አይ​ጠ​ቅ​ም​ምና፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም ግዳጅ አይ​ፈ​ጽ​ም​ምና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios