እንደገና ደግሞ ወንድ ልጅን ወለደች፤ ስሙንም ሴሎም ብላ ጠራችው፤ እነርሱንም በወለደች ጊዜ ኬሴቢ በሚባል ሀገር ነበረች።
ነህምያ 11:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሴሎ ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ፥ የዮያሪብ ልጅ፥ የዓዳያ ልጅ፥ የዖዝያ ልጅ፥ የኮልሖዜ ልጅ፥ የባሩክ ልጅ መዕሤያ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሴሎ ዘር የዘካርያስ ልጅ፣ የዮያሪብ ልጅ፣ የዓዳያ ልጅ፣ የፆዛያ ልጅ፣ የኮልሖዜ ልጅ፣ የባሮክ ልጅ መዕሤያ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሺሎናዊው ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ የዮያሪብ ልጅ፥ የዓዳያ ልጅ፥ የሐዛያ ልጅ፥ የኮልሖዜ ልጅ፥ የባሩክ ልጅ ማዓሤያ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኮልሖዜ የልጅ ልጅ የሆነው የባሩክ ልጅ ማዕሤያ ሌሎች የቀድሞ አባቶቹ የይሁዳ ልጅ የነበረው የሼላ ዘሮች የሆኑትን ሐዛያን፥ ዓዳያን፥ የዮያሪብንና ዘካርያስን ይጨምራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሴሎናዊውም ልጅ የዘካርያስ ልጅ የዮያሪብ ልጅ የዓዳያ ልጅ የዖዛያ ልጅ የኮልሖዜ ልጅ የባሮክ ልጅ መዕሤያ። |
እንደገና ደግሞ ወንድ ልጅን ወለደች፤ ስሙንም ሴሎም ብላ ጠራችው፤ እነርሱንም በወለደች ጊዜ ኬሴቢ በሚባል ሀገር ነበረች።
ከይሁዳና ከብንያምም ልጆች እነዚህ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። ከይሁዳ ልጆች፤ ከፋሬስ ልጆች የመላልኤል ልጅ፥ የሰፋጥያስ ልጅ፥ የሰማርያ ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ፥ የዖዝያ ልጅ አታያ፤
የመሴፋም ገዢ የኮልሐዜ ልጅ ሰሎም የምንጩን በር አደሰ፤ ሠራው፤ ከደነውም፤ ሳንቃዎቹንም አቆመ፤ ቍልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረገ፤ ከዳዊትም ከተማ እስከሚወርደው ደረጃ ድረስ በንጉሡ አትክልት አጠገብ ያለውን የመዋኛ ቅጥር ሠራ።