ነህምያ 11:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዓናቶት፥ በኖብ፥ በሐናንያ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዓናቶት፣ በኖብና በሐናንያ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓናቶት፥ ኖብ፥ አናንያ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐናቶት፥ ኖብ፥ ዓናንያ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቤቴልና በመንደሮችዋ፥ በዓናቶት፥ በኖብ፥ |
በብንያም ሀገር በዓናቶት ከነበሩ ካህናት ወገን ወደ ሆነ ወደ ኬልቅያስ ልጅ ወደ ኤርምያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል።
ዳዊትም ወደ ካህኑ ወደ አቤሜሌክ ወደ ኖብ መጣ፤ አቤሜሌክም እርሱን በተገናኘው ጊዜ ደነገጠ፥ “ስለምን አንተ ብቻህን ነህ? ከአንተስ ጋር ስለምን ማንም የለም?” አለው።
ዳዊትም ካህኑን አቤሜሌክን፥ “የተላክህበትን ነገርና የሰጠሁህን ትእዛዝ ማንም አይወቅ ብሎ ንጉሡ አንድ ነገር አዝዞኛል፤ ስለዚህም ‘ብላቴኖቼን በእግዚአብሔር መታመን’ በሚባለው እንዲህ ባለው ስፍራ እንዲሆኑ አዝዣቸዋለሁ።
የካህናቱንም ከተማ ኖብን በሰይፍ ስለት መታ፤ ወንዶችንና ሴቶችንም፥ ብላቴኖችንና ጡት የሚጠቡትን፥ በሬዎችንና አህዮችንም፥ በጎችንም በሰይፍ ስለት ገደለ።