ማቴዎስ 12:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ለሕዝቡ ሲናገር ሳለ፣ እናቱና ወንድሞቹ ሊያነጋግሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሕዝቡ ይህን እየተናገረ ሳለ፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ለሕዝቡ ገና ሲናገር ሳለ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊያነጋግሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር። [ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር። |
ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።
ይህስ ጸራቢው የማርያም ልጅ የያቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምዖንም ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ በዚህ በእኛ ዘንድ አይደሉምን?” አሉ፤ ይሰናከሉበትም ነበር።
ስምዖንም ባረካቸው፤ እናቱን ማርያምንም እንዲህ አላት፤ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን ከእስራኤል መካከል ለብዙዎች ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው፥ ለሚቃወሙትም ምልክት ይሆን ዘንድ የተሠየመ ነው፤
በአዩትም ጊዜ ደነገጡ፤ እናቱም፥ “ልጄ፥ ለምን እንዲህ አደረግኸን? እነሆ አባትህም፥ እኔም ስንፈልግህ ደከምን” አለችው።
ከእነርሱም ጋር ሂዶ ወደ ናዝሬት ወረደ፤ ይታዘዝላቸውም ነበር፤ እናቱ ግን ይህን ሁሉ ነገር ትጠብቀው፥ በልብዋም ታኖረው ነበር።
እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ለእናንተ ተሰጥቶአችኋል፤ ለእነዚያ ግን አይተው እንዳያዩ፥ ሰምተውም እንዳይሰሙ፥ እንዳያስተውሉም በምሳሌ ነው።
በጌታችን በኢየሱስ መስቀል አጠገብም እናቱ፥ የእናቱም እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊት ማርያምም ቆመው ነበር።
ከዚህም በኋላ እርሱና እናቱ፥ ወንድሞቹና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ቅፍርናሆም ወረዱ፤ በዚያም ብዙ ያይደለ ጥቂት ቀን ተቀመጡ።
ወንድሞቹም ጌታችን ኢየሱስን እንዲህ አሉት- “ደቀ መዛሙርትህ የምትሠራውን ሥራህን እንዲያዩ ከዚህ ወጥተህ ወደ ይሁዳ ሀገር ሂድ።