ማርቆስ 8:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ በሽማግሌዎችም በካህናት አለቆችም በጻፎችም ሊናቅ፥ ሊገደልም ከሦስት ቀንም በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የሰው ልጅ ብዙ መከራ እንደሚቀበል፣ በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጸሐፍት እንደሚናቅ፣ እንደሚገደል፣ ከሦስት ቀንም በኋላ እንደሚነሣ ያስተምራቸው ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም የሰው ልጅ ብዙ መከራ እንደሚቀበል፥ በሽማግሌዎች፥ በካህናት አለቆችና በጸሐፍት እንደሚናቅ፥ እንደሚገደል፥ ከሦስት ቀንም በኋላ እንደሚነሣ ያስተምራቸው ጀመር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ሲል ማስተማር ጀመረ፤ “የሰው ልጅ ብዙ መከራ መቀበል ይገባዋል፤ በሽማግሌዎች፥ በካህናት አለቆችና በሕግ መምህራን ዘንድ ይናቃል፤ ይገደላልም፤ ይሁን እንጂ ከሦስት ቀን በኋላ ይነሣል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል፥ ሊገደልም ከሦስት ቀንም በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር። |
መልኩም የተናቀ፥ ከሰውም ልጆች ሁሉ የተዋረደ፥ የተገረፈ ሰው፥ መከራንም የተቀበለ ነው፤ ፊቱንም መልሶአልና አቃለሉት፥ አላከበሩትምም።
ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፤’ የሚለውን ከቶ በመጽሐፍ አላነበባችሁምን?
‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው።’ የሚለውን ይህን መጽሐፍ አላነበባችሁምን?”
እርሱም፥ “በሙሴ ኦሪት፥ በነቢያትና በመዝሙርም ስለ እኔ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ እንዳለው፥ ከእናንተ ጋር ሳለሁ የነገርኋችሁ ነገሬ ይህ ነው” አላቸው።
የሚክደኝን፥ ቃሌንም የማይቀበለውን ግን የሚፈርድበት አለ፤ እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ በመጨረሻዪቱ ቀን ይፈርድበታል።
“በእኛ ላይ አለቃና ፈራጅ ማን አድርጎሃል? ብለው የካዱትን ያን ሙሴን በቍጥቋጦው መካከል በታየው በመልአኩ እጅ እርሱን መልእክተኛና አዳኝ አድርጎ እግዚአብሔር ላከው።
ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቃችሁ ሁሉ ያዳናችሁን እግዚአብሔርን ንቃችሁ፦ ‘እንዲህ አይሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁት። አሁንም በየነገዳችሁና በየወገናችሁ በእግዚአብሔር ፊት ቁሙ” አላቸው።
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን አለው፥ “በእነርሱ ላይ እንዳልነግሥ እኔን ናቁ እንጂ አንተን አልናቁምና በሚሉህ ነገር ሁሉ የሕዝቡን ቃል ስማ።