ታዳጊህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሕይወቱን የሚያስጨንቃትን፥ በአሕዛብ የተጠላውን የአለቆችን ባርያ ቀድሱት፤ ነገሥታት ያዩታል፤ አለቆችም ስለ እግዚአብሔር ብለው ተነሥተው ይሰግዱለታል፤ የእስራኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መርጨሃለሁና።”
ማርቆስ 6:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህስ ጸራቢው የማርያም ልጅ የያቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምዖንም ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ በዚህ በእኛ ዘንድ አይደሉምን?” አሉ፤ ይሰናከሉበትም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ዐናጺው አይደለምን? የማርያም ልጅ፣ የያዕቆብ፣ የዮሴፍ፣ የይሁዳና የስምዖን ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ እዚሁ እኛው ዘንድ አይደሉምን?” ከዚህም የተነሣ ተሰናከሉበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ዐናጢው አይደለምን? የማርያም ልጅ፥ የያዕቆብና የዮሳ፥ የይሁዳና የስምዖን ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ እዚሁ እኛው ዘንድ አይደሉምን?” ከዚህም የተነሣ ተሰናከሉበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥለውም “ለመሆኑ ይህ እንጨት ጠራቢው የማርያም ልጅ አይደለምን? የያዕቆብ፥ የዮሳ የይሁዳና የስምዖን ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ እዚህ ከእኛ ጋር አይደሉምን?” እያሉ በመናቅ ሳይቀበሉት ቀሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህስ ጸራቢው የማርያም ልጅ የያቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምዖንም ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ በዚህ በእኛ ዘንድ አይደሉምን? አሉ፤ ይሰናከሉበትም ነበር። |
ታዳጊህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሕይወቱን የሚያስጨንቃትን፥ በአሕዛብ የተጠላውን የአለቆችን ባርያ ቀድሱት፤ ነገሥታት ያዩታል፤ አለቆችም ስለ እግዚአብሔር ብለው ተነሥተው ይሰግዱለታል፤ የእስራኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መርጨሃለሁና።”
ሴቶችም ደግሞ በሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበር፤ ከእነርሱም በገሊላ ሳለ ይከተሉትና ያገለግሉት የነበሩ መግደላዊት ማርያም የታናሹ ያዕቆብና የዮሳም እናት ማርያም ሰሎሜም ነበሩ፤
ስምዖንም ባረካቸው፤ እናቱን ማርያምንም እንዲህ አላት፤ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን ከእስራኤል መካከል ለብዙዎች ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው፥ ለሚቃወሙትም ምልክት ይሆን ዘንድ የተሠየመ ነው፤
የአስቆሮቱ ሰው ያይደለ ይሁዳም፥ “ጌታ ሆይ፥ ለዓለም ያይደለ ለእኛ ራስህን ትገልጥ ዘንድ እንዳለህ የተናገርኸው ምንድን ነው?” አለው።
“እኛ አባቱንና እናቱን የምናውቃቸው ይህ የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ አይደለምን? እንግዲህ እንዴት ከሰማይ ወረድሁ ይለናል?” አሉ።
ወደ ማደሪያቸውም በደረሱ ጊዜ ጴጥሮስ፥ ዮሐንስ፥ ያዕቆብ፥ እንድርያስ፥ ፊልጶስ፥ ቶማስ፥ ማቴዎስ፥ በርተሎሜዎስ፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፥ ቀናተኛው ስምዖን፥ የያዕቆብ ልጅ ይሁዳም ወደሚኖሩበት ሰገነት ወጡ።
እርሱ ግን ዝም እንዲሉ በእጁ አመለከታቸው፤ ከወኅኒ ቤትም እግዚአብሔር እንደ አወጣው ነገራቸው፤ “ይህንም ለያዕቆብና ለወንድሞች ሁሉ ንገሩ” አላቸው፤ ከዚያም ወጥቶ ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።