ሉቃስ 5:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ሙሽራውን ከእነርሱ የሚወስዱበት ቀን ይመጣል፤ ያንጊዜም ይጾማሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤ በእነዚያም ጊዜያት ይጾማሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ቀኖች ይመጣሉ፤ በነዚያ ቀኖች ይጾማሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ይጾማሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ወራት ይመጣል፥ ሙሽራውም ከእነርሱ ሲወሰድ ያንጊዜ፥ በዚያ ወራት ይጦማሉ አላቸው። |
ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፣ እጄንም በታናናሾች ላይ እመልሳለሁ።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።
ደቀ መዛሙርቱንም እንዲህ አላቸው፥ “ከሰው ልጆች ቀኖች አንዲቱን ታዩ ዘንድ የምትመኙበት ወራት ይመጣል፤ ነገር ግን አታዩአትም።
በምሳሌም እንዲህ አላቸው፥ “በአሮጌ ልብስ ቀዳዳ ላይ የአዲስ ልብስ እራፊ የሚጥፍ የለም፤ ያለዚያ ግን አዲሱ አሮጌውን ይቀድደዋል፤ አዲሱ እራፊም ከአሮጌው ጋር አይስማማም።
ድሆች ግን ዘወትር አብረዋችሁ አሉ፤ ዘወትርም ታገኙአቸዋላችሁ፤ በወደዳችሁም ጊዜ መልካም ታደርጉላቸዋላችሁ፤ እኔን ግን ዘወትር የምታገኙኝ አይደለም።”
ልጆች ሆይ፥ ገና ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር አለሁ፤ ትሹኛላችሁ፤ ለአይሁድም እኔ ወደምሄድበት እናንተ መምጣት አይቻላችሁም እንዳልኋቸው፥ አሁንም ለእናንተ እነግራችኋለሁ።
ይህንም እየነገራቸው ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ተቀበለችው፤ እነርሱም ወደ እርሱ እያዩ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ከዐይናቸውም ተሰወረ።
እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እስከ ተናገረው የመደራጀት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀበለው ዘንድ ይገባል።
ለጸሎት እንድትተጉ ከምትስማሙበት ጊዜ ብቻ በቀር፥ ባልና ሚስት አትለያዩ፤ ዳግመኛ ሰይጣን ድል እንዳያደርጋችሁ በአንድነት ኑሩ፤ ሰውነታችሁ ደካማ ነውና ።
በድካምና በጥረት፥ ብዙ ጊዜም ዕንቅልፍ በማጣት፥ በመራብና በመጠማት፥ አብዝቶም በመጾም፥ በብርድና በመራቆት ተቸገርሁ።