“እኔ ንጹሕ ነኝና ከእኔ ራቁ፥ ወደ እኔም አትቅረቡ” ይላሉ። ስለዚህም የቍጣዬ ጢስ በዘመኑ ሁሉ እንደ እሳት ይነድድባቸዋል።
ሉቃስ 15:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተቈጥቶም ‘አልገባም’ አለ፤ አባቱም ወጥቶ ማለደው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ታላቅ ወንድሙም ተቈጣ፤ ወደ ቤትም መግባት አልፈለገም፤ አባቱም ወደ ውጭ ወጥቶ እንዲገባ ለመነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ተቈጣ፤ ሊገባም አልፈለገም፤ አባቱም ወጥቶ ለመነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ታላቅ ወንድሙም በጣም ተቈጥቶ፥ ‘ወደ ቤት አልገባም’ አለ። ስለዚህ አባቱ ወደ ደጅ ወጥቶ እንዲገባ ለመነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተቈጣም ሊገባም አልወደደም፤ አባቱም ወጥቶ ለመነው። |
“እኔ ንጹሕ ነኝና ከእኔ ራቁ፥ ወደ እኔም አትቅረቡ” ይላሉ። ስለዚህም የቍጣዬ ጢስ በዘመኑ ሁሉ እንደ እሳት ይነድድባቸዋል።
በቃሉ የምትንቀጠቀጡ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ “የእግዚአብሔር ስም ይከብር ዘንድ፦ ደስታችሁም ይገለጥ ዘንድ፥ እነርሱም ያፍሩ ዘንድ የሚጠሏችሁንና የሚጸየፉአችሁን ወንድሞቻችን በሏቸው።
እግዚአብሔርም ዮናስን፥ “በውኑ ስለዚች ቅል ታዝናለህን?” አለው። እርሱም፥ “እስክሞት ድረስ እጅግ አዝኛለሁ” አለ።
ተቀብለውም ‘እነዚህ ኋለኞች አንድ ሰዓት ሠሩ፤ የቀኑንም ድካምና ትኩሳት ከተሸከምን ከእኛ ጋር አስተካከልሃቸው፤’ ብለው በባለቤቱ ላይ አንጕኦራጕኦሩ።
“ነቢያትን የምትገድሊያቸው፥ ወደ አንቺ የተላኩትን ሐዋርያትንም የምትደበድቢያቸው ኢየሩሳሌም፥ ኢየሩሳሌም፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፍዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን ልሰበስባቸው ምን ያህል ወደድሁ? ነገር ግን እንቢ አላችሁ።
መልሶም አባቱን እንዲህ አለው፦ ‘እነሆ፥ ይህን ያህል ዓመት ተገዛሁልህ፤ ፈጽሞ ከትእዛዝህ አልወጣሁም፤ ለእኔ ግን ከባልንጀሮች ጋር ደስ እንዲለኝ አንድ የፍየል ጠቦት እንኳ አልሰጠኸኝም።
ጻፎችና ፈሪሳውያንም፥ “ከቀራጮችና ከኃጥኣን ጋር ለምን ትበላላችሁ? ትጠጡማላችሁ?” ብለው በደቀ መዛሙርቱ ላይ አንጐራጐሩ።
የጠራው ፈሪሳዊም ባየ ጊዜ በልቡ ዐሰበ፤ እንዲህም አለ፥ “ይህስ ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህቺ የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እንዴትስ እንደ ነበረች ባላወቀም ነበርን? ኀጢአተኛ ናትና።”
አይሁድ ግን እግዚአብሔርን የሚፈሩ የከበሩ ሴቶችንና የከተማውን ሽማግሌዎች አነሳሡአቸው፤ በጳውሎስና በበርናባስ ላይም ስደትን አስነሡ፤ ከሀገራቸውም አባረሩአቸው።
አይሁድም ከአንጾኪያና ከኢቆንያ መጡ፤ ልባቸውንም እንዲያጠኑባቸው አሕዛብን አባበሉአቸው፤ ጳውሎስንም እየጐተቱ ከከተማ ውጭ አውጥተው በድንጋይ ደበደቡት፤ የሞተም መሰላቸው።
እስራኤል ብቻ አልሰሙምን? ሙሴስ አስቀድሞ እንዲህ ብሎአቸው የለምን? “እኔ በማያስተውሉ ወገኖች አስቀናቸዋለሁ፤ ወገን ባልሆነውም አስቈጣቸዋለሁ።”
እኛስ በክርስቶስ አምሳል እንለምናለን፤ እግዚአብሔርም በእኛ መጽናናትን ይሰጣችኋል፤ ከእግዚአብሔርም ጋር ትታረቁ ዘንድ በክርስቶስ እንለምናችኋለን።
ታላቅ ወንድሙም ኤልያብ ከሰዎች ጋር ሲነጋገር ሰማ፤ ኤልያብም በዳዊት ላይ እጅግ ተቈጣ፥ “ለምን ወደዚህ ወረድህ? እነዚያንስ ጥቂቶች በጎች በምድረ በዳ ለማን ተውሃቸው? እኔ ኵራትህንና የልብህን ክፋት አውቃለሁና ሰልፉን ለማየት መጥተሃል” አለው።
ሳኦልም እጅግ ተቈጣ፤ ይህም ነገር ሳኦልን አስከፋው፤ እርሱም፥ “ለዳዊት ዐሥር ሺህ ሰጡት፤ ለእኔ ግን ሺህ ብቻ ሰጡኝ፤ ከመንግሥት በቀር ምን ቀረበት?” አለ።