ጐልማሳም ከድንግሊቱ ጋር እንደሚኖር፥ እንዲሁ ልጆችሽ ከአንቺ ጋር ይኖራሉ፤ ሙሽራም በሙሽራዪቱ ደስ እንደሚለው፥ እንዲሁ አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል።
ሉቃስ 12:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታቸው በመጣ ጊዜ እንዲህ ሲያደርጉና ሲተጉ የሚያገኛቸው አገልጋዮች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ወገቡን ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል፤ እየተመላለሰም ያገለግላቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታቸው በሚመጣበት ጊዜ ነቅተው የሚያገኛቸው ባሮች ብፁዓን ናቸው። እውነት እላችኋለሁ፤ ጌታቸውም በዐጭር ይታጠቃል፤ በማእድ ያስቀምጣቸዋል፤ ቀርቦም ያስተናግዳቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባርያዎች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል፤ ቀርቦም ያገለግላቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚያ ጌታቸው ድንገት በመጣ ጊዜ፥ ነቅተው ሲጠብቁ የሚያገኛቸው አገልጋዮች እንዴት የተመሰገኑ ናቸው? በእውነት እላችኋለሁ፤ እርሱ ባጭር ታጥቆ በማእድ ያስቀምጣቸዋል፤ ቀርቦም ያገለግላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል ቀርቦም ያገለግላቸዋል። |
ጐልማሳም ከድንግሊቱ ጋር እንደሚኖር፥ እንዲሁ ልጆችሽ ከአንቺ ጋር ይኖራሉ፤ ሙሽራም በሙሽራዪቱ ደስ እንደሚለው፥ እንዲሁ አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል።
ለእነርሱም መልካምን በማድረግ ይቅር እላቸዋለሁ፤ በእውነትም በፍጹም ልቤና በፍጹም ነፍሴ በዚህች ምድር እተክላቸዋለሁ።
አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፣ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል።
እናንተም፥ በመጣና በር በመታ ጊዜ ወዲያው ይከፍቱለት ዘንድ ከሰርግ እስኪመለስ ጌታቸውን እንደሚጠብቁ ሰዎች ሁኑ።
እራቴን አዘጋጅልኝ፥ እስክበላና እስክጠጣ ድረስም ታጥቀህ አሳልፍልኝ፤ ከዚህም በኋላ አንተ ብላ፥ ጠጣም ይለው የለምን?
የሚበልጥ ማንኛው ነው? በማዕድ ላይ የተቀመጠው ነው? ወይስ የሚላላከው? በማዕድ ላይ የተቀመጠው አይደለምን? እነሆ፥ እኔ በመካከላችሁ እንደ አገልጋይ ነኝ።
እኔን የሚያገለግለኝ ካለ ይከተለኝ፤ የሚያገለግለኝ እኔ ባለሁበት በዚያ ይኖራልና፤ እኔን የሚያገለግለኝንም አብ ያከብረዋል።
ነገር ግን መጽሐፍ፥ “ዐይን ያላየው፥ ጆሮም ያልሰማው፥ በሰውም ልቡና ያልታሰበ እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ነው።” ብሎ የለምን?
በእነዚህ በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ እኔስ ከዚህ ዓለም ልለይ፥ በከክርስቶስም ዘንድ ልኖር እወዳለሁ፤ ይልቁንም ለእኔ ይህ ይሻለኛል፤ ይበልጥብኛልም።
ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ። “ይህንን ጻፍ፡ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው።” መንፈስም “አዎን! ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸውም ይከተላቸዋል፤” ይላል።
በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፤ ወደ ሕይወትም ውሃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል።”