Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 2:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ነገር ግን መጽ​ሐፍ፥ “ዐይን ያላ​የው፥ ጆሮም ያል​ሰ​ማው፥ በሰ​ውም ልቡና ያል​ታ​ሰበ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ወ​ዱት ያዘ​ጋ​ጀው ነው።” ብሎ የለ​ምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ይሁን እንጂ እንደ ተጻፈው፣ “ዐይን ያላየውን፣ ጆሮ ያልሰማውን፣ የሰውም ልብ ያላሰበውን፣ እግዚአብሔር ለሚወድዱት አዘጋጅቷል፤”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ነገር ግን እንደተጻፈው፥ “ዐይን ያላየውን፤ ጆሮም ያልሰማው፤ በሰውም ልብ ያልታሰበው፤ እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው፤”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ይሁን እንጂ መጽሐፍ፥ “የሰው ዐይን ያላየውን፥ የሰው ጆሮ ያልሰማውን፥ የሰው ልብ ያላሰበውን፥ እግዚአብሔር ለሚወዱት አዘጋጅቶአል” ይላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ነገር ግን፦ ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 2:9
12 Referencias Cruzadas  

ከጥ​ንት ጀምሮ ይቅ​ር​ታ​ህን ለሚ​ጠ​ባ​በቁ ምሕ​ረ​ትን ከም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ቸው ከአ​ንተ በቀር ሌላ አም​ላክ አላ​የ​ንም፤ አል​ሰ​ማ​ን​ምም።


በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ዱ​ትን ምር​ጦ​ቹን በበጎ ምግ​ባር ሁሉ እን​ደ​ሚ​ረ​ዳ​ቸው እና​ው​ቃ​ለን።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለ ጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?


“እነሆ፥ አዲስ ሰማ​ይና አዲስ ምድር ይሆ​ና​ልና፤ የቀ​ደ​ሙ​ትም አይ​ታ​ሰ​ቡም፤ ወደ ልብም አይ​ገ​ቡም።


አሁን ግን፥ በሰ​ማ​ያት ያለ​ች​ውን የም​ት​በ​ል​ጠ​ውን ሀገር ተስፋ ያደ​ርጉ እንደ ነበር ታወቀ፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው ተብሎ ይጠራ ዘንድ በእ​ነ​ርሱ አያ​ፍ​ርም፤ ተስፋ ያደ​ረ​ጉ​አ​ትን ሀገር አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ላ​ቸ​ዋ​ልና።


ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል ‘እናንተ የአባቴ ቡሩካን! ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።


እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።


በእ​ርሱ የሚ​ያ​ምን ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እን​ዲ​ያ​ገኝ እንጂ እን​ዳ​ይ​ጠፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አን​ድያ ልጁን ቤዛ አድ​ርጎ እስ​ኪ​ሰጥ ድረስ ዓለ​ሙን እን​ዲህ ወዶ​ታ​ልና።


ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።


እርሱም “ጽዋዬንስ ትጠጣላችሁ፤ በቀኝና በግራ መቀመጥ ግን ከአባቴ ዘንድ ለተዘጋጀላቸው ነው እንጂ እኔ የምሰጥ አይደለሁም፤” አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios