አሮንም ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በተናገረ ጊዜ ወደ ምድረ በዳ ፊታቸውን አቀኑ፤ እነሆም፥ የእግዚአብሔር ክብር በደመናው ታየ።
ዘሌዋውያን 9:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለደኅንነትም መሥዋዕት በሬንና አውራ በግን፥ በዘይትም የተለወሰ የእህልን ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይሠዉ ዘንድ ውሰዱ፤ ዛሬ እግዚአብሔር ይገለጥላችኋልና ብለህ ንገራቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለኅብረት መሥዋዕት አንድ በሬና አንድ አውራ በግ በዘይት ከተለወሰ የእህል ቍርባን ጋራ በእግዚአብሔር ፊት ለመሠዋት አቅርቡ፤ እግዚአብሔር ዛሬ ይገለጥላችኋልና።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአንድነትም መሥዋዕት በሬንና አውራን በግ፥ በዘይትም የተለወሰ የእህልን ቁርባን በጌታ ፊት ለመሠዋት ውሰዱ፥ ዛሬ ጌታ ተገልጦላችኋልና።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም አንድ ወይፈንና አንድ የበግ ጠቦት ለአንድነት መሥዋዕት ያምጡ፤ እነዚህንም በዘይት ከታሸ የእህል መባ ጋር ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡ፤ ዛሬ እግዚአብሔር ስለሚገለጥላቸው ይህን ሁሉ ያድርጉ።” |
አሮንም ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በተናገረ ጊዜ ወደ ምድረ በዳ ፊታቸውን አቀኑ፤ እነሆም፥ የእግዚአብሔር ክብር በደመናው ታየ።
በሦስተኛውም ቀን ሕዝቡ ሁሉ ሲያዩ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ይወርዳልና ለሦስተኛው ቀን ተዘጋጅተው ይጠብቁ።
የእግዚአብሔርም ክብር በሲና ተራራ ላይ ወረደ፤ ደመናውም ስድስት ቀን ሸፈነው፤ በሰባተኛውም ቀን እግዚአብሔር ከደመናው ውስጥ ሙሴን ጠራው።
እነሆም የእስራኤል አምላክ ክብር ከምሥራቅ መንገድ መጣ፤ ድምፁም እንደ ብዙ ውኆች ይተምም ነበር፤ ከክብሩም የተነሣ ምድር ታበራ ነበር።
ቀኖቹንም በፈጸሙ ጊዜ በስምንተኛው ቀን ከዚያም በኋላ ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ የደኅንነት መሥዋዕታችሁንም በመሠዊያው ላይ ያደርጋሉ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
“ማናቸውም ሰው ቍርባን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዲሆን ቢያቀርብ፥ ቍርባኑ ከመልካም ስንዴ ዱቄት ይሁን፤ ዘይትም ያፈስስበታል፤ ነጭ ዕጣንም ይጨምርበታል፤ ይህም መሥዋዕት ነው።
“ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ቍርባን የደኅንነት መሥዋዕት ቢሆን፥ ከላሞች መንጋ ተባት ወይም እንስት ቢያቀርብ፥ ነውር የሌለበትን በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ።
የእስራኤልንም ልጆች፦ ለኀጢአት መሥዋዕት አውራ ፍየልን፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን አንድ ዓመት የሆናቸውን ጥጃና ጠቦትን፥
ማኅበሩ ሁሉ ግን “በድንጋይ እንውገራቸው” አሉ። የእግዚአብሔርም ክብር ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በምስክሩ ድንኳን ተገለጠ።