ዘሌዋውያን 6:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይም በሐሰት የማለበትን ነገር ቢመልስ፥ በሙሉ ይመልስ፤ ከዚያም በላይ አምስተኛውን ክፍል ጨምሮ የበደሉን መሥዋዕት በሚያቀርብበት ቀን ለባለ ገንዘቡ ይስጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሐሰት የማለበትንም ሁሉ ይመልስ፤ የበደል መሥዋዕቱን በሚያቀርብበት ጊዜ የወሰደውን በሙሉ የዋናውን አንድ ዐምስተኛ በመጨመር ለባለንብረቱ ንብረቱ ይመልስ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይም በሐሰት የማለበትን ምንም ዓይነት ነገር ይመልስ፤ እርሱም የበደሉን መሥዋዕት በሚያቀርብበት ቀን በሙሉ የወሰደውን ነገር ይመልስ፥ በእርሱም ላይ አምስት እጅ ጨምሮበት ለባለቤቱ ይስጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወይም በሐሰት ምሎ የወሰደውን ሁሉ አንድ አምስተኛ ጨምሮ ለባለቤቱ ይክፈል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይም በሐሰት የማለበትን ነገር ይመልስ፤ በሙሉ ይመልስ፥ ከዚያም በላይ አምስተኛውን ክፍል ጨምሮ የበደሉን መሥዋዕት በሚያቀርብበት ቀን ለባለ ገንዘቡ ይስጠው። |
በየዓመቱም የመሬታችንን እህል ቀዳምያት፥ የሁሉ ዓይነት ዛፍ የፍሬ ቀዳምያት ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣ ዘንድ፥
“ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅ፥ ቢያርደው ወይም ቢሸጠው፥ በአንድ በሬ ፋንታ አምስት በሬዎች፥ በአንድ በግም ፋንታ አራት በጎች ይክፈል።
“ሰው በባልንጀራው ዘንድ ብር ወይም ሌላ ዕቃ እንዲጠብቅለት አደራ ቢያኖር ከቤቱም ቢሰረቅ፥ ሌባው ቢገኝ እጥፍ ይክፈል።
ሰዎች ስለ በሬ ወይም ስለ አህያ ወይም ስለ በግ ወይም ስለ ልብስ ወይም ስለሌላ ስለ ጠፋ ነገር ቢካሰሱ፥ አንዱም፦ ‘ይህ የእኔ ነው’ ቢል፥ ክርክራቸው በፈጣሪ ፊት ይቅረብ፤ በፈጣሪ ፊት የተፈረደበት እርሱ ለባልንጀራው እጥፍ ይክፈል።
ይህን ጾም የመረጥሁ አይደለም ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን የበደልን እስራት ፍታ፤ ጠማማውን ሁሉ አቅና፤ የተጨነቀውንም ሁሉ አድን፤ የዐመፃ ደብዳቤንም ተው።
ያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ፤ እርሱም፦ እነሆኝ፥ ይልሃል። የዐመፅ እስራትን ከመካከልህ ብታርቅ፥ ጣትህንም መጥቀስ ማንጐራጐርንም ብትተው፥
ኀጢአተኛውም መያዣን ቢመልስ፥ የነጠቀውንም ቢከፍል፥ በሕይወትም ትእዛዝ ቢሄድ፥ ኀጢአትም ባይሠራ፥ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም።
በተቀደሰ ነገር ላይ ስለ ሠራው ኀጢአት ዕዳ ይከፍላል፤ አምስተኛውንም እጅ ይጨምርበታል፤ ለካህኑም ይሰጠዋል። ካህኑም በበደል መሥዋዕት አውራ በግ ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይቅር ይባልለታል።
ዘኬዎስም ቆመና ጌታችንን እንዲህ አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አሁን የገንዘቤን እኩሌታ ለነዳያን እሰጣለሁ፤ የበደልሁትም ቢኖር ስለ አንድ ፋንታ አራት እጥፍ እከፍለዋለሁ።”
እነሆኝ፥ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንንስ አህያ ወሰድሁ? ማንንስ ሸነገልሁ? በማንስ ላይ ግፍ አደረግሁ? ነጠላ ጫማ እንኳን ቢሆን ከማን እጅ መማለጃ ተቀበልሁ? መስክሩብኝ፤ እኔ እመልስላችኋለሁ።”