La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 4:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወይ​ፈ​ኑን ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ አመድ ወደ​ሚ​ፈ​ስ​ስ​በት ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ በዕ​ን​ጨ​ትም ላይ በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​ታል፤ አመድ በሚ​ፈ​ስ​ስ​በት ስፍራ ይቃ​ጠ​ላል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የወይፈኑን ብልት ሁሉ ከሰፈር ውጭ ዐመድ ወደሚፈስስበት በአምልኮው ሥርዐት መሠረት ንጹሕ ወደ ሆነው ስፍራ ይውሰደው፤ በተቈለለው ዐመድ ላይ ዕንጨት አንድዶ ያቃጥለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወይፈኑን ሁሉ ከሰፈሩ ውጭ አመድ ወደሚፈስበት ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወስዳል፥ በእንጨትም ላይ በእሳት ያቃጥለዋል፤ አመድ በሚፈስስበት ስፍራ ይቃጠላል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከሰፈር ውጪ ያውጣ፤ ዐመድ ወደሚፈስበት ርኩስ ወዳልሆነ ስፍራ በመውሰድ እንጨት ሰብስቦ ያንድድና በእሳት ያቃጥለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፈርሱንም፥ ወይፈኑን ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ አመድ ወደሚፈስስበት ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወስደዋል፥ በእንጨትም ላይ በእሳት ያቃጥለዋል፤ አመድ በሚፈስስበት ስፍራ ይቃጠላል።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 4:12
16 Referencias Cruzadas  

የወ​ይ​ፈ​ኑን ሥጋ ግን፥ ቍር​በ​ቱ​ንም፥ ፈር​ሱ​ንም ከሰ​ፈር ውጭ በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ለ​ዋ​ለህ፤ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና።


ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን ወይ​ፈን ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ በመ​ቅ​ደ​ሱም ውጭ በቤቱ በተ​ለ​የው ስፍራ ይቃ​ጠ​ላል።


ደዌው ባለ​በት ዘመን ሁሉ ርኩስ ይሆ​ናል፤ እርሱ ርኩስ ነው፤ ብቻ​ውን ይቀ​መ​ጣል፤ መኖ​ሪ​ያ​ውም ከሰ​ፈር በውጭ ይሆ​ናል።


ለማ​ስ​ተ​ስ​ረ​ያም እን​ዲ​ሆን ደማ​ቸው ወደ መቅ​ደስ የገ​ባ​ውን የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ንና የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ያወ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ ቍር​በ​ታ​ቸ​ው​ንም፥ ሥጋ​ቸ​ው​ንም፥ ፈር​ሳ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ።


ወይ​ፈ​ኑ​ንም ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ የፊ​ተ​ኛ​ው​ንም ወይ​ፈን እን​ዳ​ቃ​ጠሉ ያቃ​ጥ​ሉ​ታል፤ የማ​ኅ​በሩ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና።


ካህ​ና​ትም የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የእ​ህል ቍር​ባን ሁሉ ፈጽሞ ይቃ​ጠ​ላል፤ ከእ​ር​ሱም አን​ዳች አይ​በ​ላም።”


ነገር ግን በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ለማ​ስ​ተ​ስ​ረያ ይሆን ዘንድ ከደሙ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን የሚ​ገ​ባው የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁሉ አይ​በ​ላም፤ በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላል።


እርሱ ቢበ​ድ​ልና ከዚህ በኋላ ንስሓ ቢገባ፥ በቅ​ድ​ሚያ የወ​ሰ​ደ​ውን፥ ወይም በዐ​መ​ፅና በግፍ የተ​ቀ​በ​ለ​ውን፥ ወይም የተ​ሰ​ጠ​ውን አደራ፥ ወይም ጠፍቶ ያገ​ኘ​ውን፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ወይ​ፈ​ኑን፥ ቍር​በ​ቱ​ንም፥ ሥጋ​ው​ንም፥ ፈር​ሱ​ንም ከሰ​ፈሩ ውጭ በእ​ሳት አቃ​ጠለ።


ሥጋ​ው​ንና ቍር​በ​ቱ​ንም ከሰ​ፈሩ ውጭ በእ​ሳት አቃ​ጠሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “ሰው​ዬው ይገ​ደል፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት” አለው።


እር​ስ​ዋ​ንም ለካ​ህኑ ለአ​ል​ዓ​ዛር ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ፤ ከሰ​ፈር ወደ ውጭ ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወ​ስ​ዷ​ታል፤ በፊ​ቱም ያር​ዷ​ታል።


ጊደ​ሪ​ቱ​ንም በፊቱ ያቃ​ጥ​ሏ​ታል፤ ቍር​በ​ቷ​ንም፥ ሥጋ​ዋ​ንም፥ ደም​ዋ​ንም፥ ፈር​ስ​ዋ​ንም ያቃ​ጥ​ሉት።


እኔ በመ​ካ​ከሉ የማ​ድ​ር​በ​ትን ሰፈ​ራ​ቸ​ውን እን​ዳ​ያ​ረ​ክሱ ከወ​ንድ እስከ ሴት ከሰ​ፈሩ አው​ጡ​አ​ቸው።”


ሊቀ ካህ​ናቱ የሚ​ሠ​ዉ​ትን እን​ስሳ ደም ስለ ኀጢ​አት ወደ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳን ያቀ​ርብ ነበ​ርና፤ ሥጋ​ው​ንም ከሰ​ፈር ውጭ ያቃ​ጥ​ሉት ነበር።