“እስከ ሦስት ቀን ድረስ የማይመጣ ሁሉ እንደ ሽማግሎችና እንዳለቆች ምክር ከብቱ ሁሉ ይበዝበዝ፤ እርሱም ከምርኮው ጉባኤ ይለይ” ብሎ ዐዋጅ አስነገረ።
ዘሌዋውያን 27:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሻው ግን በኢዮቤልዩ ዓመት ሲወጣ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ እርሻ ይሆናል፤ ርስቱም ለካህኑ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕርሻው በኢዮቤልዩ በሚለቀቅበት ጊዜ ለእግዚአብሔር እንደ ተሰጠ ዕርሻ ተቈጥሮ ቅዱስና የካህናቱ ንብረት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሻው ግን በኢዮቤልዩ ነፃ ሲወጣ እንደ እርም ለጌታ የተቀደሰ እርሻ ይሆናል፤ ለካህኑ ርስቱ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ለቀድሞ ባለቤቱ ለመመለስ የማይችለው መሬትም በተከታዩ በኢዮቤልዩ ዓመት ለእግዚአብሔር የተለየ ቀዋሚ ንብረት እንደ ሆነ ይቀራል፤ እርሱም የካህኑ ድርሻ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሻው ግን በኢዮቤልዩ ሲወጣ እንደ እርም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ እርሻ ይሆናል፤ ርስቱ ለካህኑ ይሆናል። |
“እስከ ሦስት ቀን ድረስ የማይመጣ ሁሉ እንደ ሽማግሎችና እንዳለቆች ምክር ከብቱ ሁሉ ይበዝበዝ፤ እርሱም ከምርኮው ጉባኤ ይለይ” ብሎ ዐዋጅ አስነገረ።
የእህሉን ቍርባንና የኀጢአትን መሥዋዕት የንስሓንም መሥዋዕት ይበላሉ፤ በእስራኤልም ዘንድ እርም የሆነው ነገር ሁሉ ለእነርሱ ይሆናል።
አምሳኛውንም ዓመት ትቀድሳላችሁ፤ በምድሪቱም ለሚኖሩት ሁሉ ነጻነትን ታውጃላችሁ፤ እርሱ ለእናንተ ኢዮቤልዩ ነው፤ ሰው ሁሉ ወደ ርስቱና ወደ ወገኑ ይመለስ።
ለራሱም ዕዳውን መክፈል ባይችል፥ ሽያጩ በገዛው ሰው እጅ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ይቀመጥ፤ በኢዮቤልዩም ዓመት ይውጣ፤ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለስ።
የእግዚአብሔር የመቅሠፍቱ ቍጣ ይመለስ ዘንድ፥ ለአባቶችህም እንደ ማለላቸው ይምርህ ዘንድ፥ ይራራልህም ዘንድ፥ ያበዛህም ዘንድ፥ ርጉም ከሆነው አንዳች ነገር በእጅህ አትንካ።
ከተማዪቱም በእርስዋም ያለው ሁሉ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር እርም ይሆናሉ፤ የላክናቸውን መልእክተኞች ስለ ሸሸገች ዘማዊቱ ረዓብ፥ ከእርስዋም ጋር በቤቷ ውስጥ ያሉ ሁሉ ብቻ በሕይወት ይኖራሉ።