Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 25:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ለራ​ሱም ዕዳ​ውን መክ​ፈል ባይ​ችል፥ ሽያጩ በገ​ዛው ሰው እጅ እስከ ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ድረስ ይቀ​መጥ፤ በኢ​ዮ​ቤ​ል​ዩም ዓመት ይውጣ፤ እር​ሱም ወደ ርስቱ ይመ​ለስ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ነገር ግን ዋጋውን መመለስ ካልቻለ፣ የሸጠው ርስት እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የገዢው ንብረት ሆኖ ይቈያል፤ በኢዮቤልዩ ዓመት ለባለቤቱ ይመለሳል፤ ሰውየውም ወደ ርስቱ ይመለሳል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ለማስመለስ ግን በቂ ገንዘብ ባያገኝ፥ ሽያጩ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ በገዛው ሰው እጅ ይሆናል፤ በኢዮቤልዩ ዓመት ነፃ ይወጣል፥ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለሳል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ነገር ግን ለመዋጀት የሚያስችል በቂ ገንዘብ ባይኖረው ርስቱ እስከ ተከታዩ የኢዩቤልዩ ዓመት ድረስ በዚያው በገዛው ሰው እጅ ሊቆይለት ይችላል። በዚያም ዓመት ርስቱ ለባለቤቱ ይመለሳል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ለራሱም ዕዳውን መክፈል ባይችል፥ ሽያጩ በገዛው ሰው እጅ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ይቀመጥ፤ በኢዮቤልዩ ዓመት ይውጣ፥ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለስ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 25:28
11 Referencias Cruzadas  

የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ሰዎች በዚህ ምድር ቤት​ንና እር​ሻን የወ​ይን ቦታ​ንም እንደ ገና ይገ​ዛሉ።”


አም​ሳ​ኛ​ው​ንም ዓመት ትቀ​ድ​ሳ​ላ​ችሁ፤ በም​ድ​ሪ​ቱም ለሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ነጻ​ነ​ትን ታው​ጃ​ላ​ችሁ፤ እርሱ ለእ​ና​ንተ ኢዮ​ቤ​ልዩ ነው፤ ሰው ሁሉ ወደ ርስ​ቱና ወደ ወገኑ ይመ​ለስ።


“በዚች ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ሰው ሁሉ ወደ ርስቱ ይመ​ለ​ሳል።


“ሰውም ቅጥር ባለ​በት ከተማ መኖ​ርያ ቤትን ቢሸጥ፥ ከተ​ሸጠ በኋላ አንድ ዓመት እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ ለመ​ቤ​ዠት ይች​ላል፤ ለአ​ንድ ሙሉ ዓመት መቤ​ዠት ይች​ላል።


አንድ ዓመት እስ​ኪ​ጨ​ረስ ባይ​ቤ​ዠው ቤቱ ለገዡ ይሆ​ናል፤ ቅጥር ባለ​በት ከተማ ያለ​ውን ያን ቤት ይመ​ረ​ም​ሩ​ለ​ታል፤ ለገ​ዛው ሰው ለልጅ ልጁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጸ​ና​ለ​ታል፤ በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመ​ትም አይ​ወ​ስ​ዱ​በ​ትም።


በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመ​ትም እርሱ ከል​ጆቹ ጋር ከአ​ንተ ይወ​ጣል፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም፥ ወደ አባ​ቱም ርስት ይመ​ለ​ሳል።


በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመት እር​ሻው የም​ድ​ሪቱ ባለ ርስት ወደ ነበ​ረው ወደ ሸጠው ሰው ይመ​ለ​ሳል፤ የራሱ ወሰን ምድር ነውና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos