እንዲሁም በበሬዎችህና በበጎችህ፥ በአህያህም ታደርገዋለህ፤ ሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቀመጥ፤ በስምንተኛውም ቀን ለእኔ ትሰጠዋለህ።
ዘሌዋውያን 22:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእርሱም እንዳይረክስ፥ የሞተውን፥ አውሬም የሰበረውን አይብላ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዳይረክስ ማንኛውንም ሞቶ የተገኘውን ወይም አውሬ የዘነጠለውን አይብላ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሱም እንዳይረክስ፥ የሞተውን አውሬም የገደለውን አይብላ፤ እኔ ጌታ ነኝ።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞቶ የተገኘውን ወይም አውሬ የገደለውን የእንስሳ ሥጋ አይብላ፤ እርሱን ቢበላ ያረክሰዋል፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርሱም እንዳይረክስ፥ የሞተውን አውሬም የሰበረውን አይብላ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
እንዲሁም በበሬዎችህና በበጎችህ፥ በአህያህም ታደርገዋለህ፤ ሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቀመጥ፤ በስምንተኛውም ቀን ለእኔ ትሰጠዋለህ።
እኔም፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ይህ አግባብ አይደለም፤ እነሆ ሰውነቴ አልረከሰችም፤ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ጥንብና አውሬ የሰበረውን ከቶ አልበላሁም፤ ርኵስም ሥጋ በአፌ ውስጥ አልገባም” አልሁ።
የሞተውን ወይም አውሬ የሰበረውን የሚበላ ሰው ሁሉ፥ የሀገር ልጅ ወይም እንግዳ ቢሆን፥ ልብሱን ያጥባል፤ በውኃም ይታጠባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።
የበከተዉን ሁሉ አትብሉ፤ ይበላው ዘንድ በሀገርህ ደጅ ለተቀመጠ መጻተኛ ወይም ለባዕድ ስጠው፤ አንተ ለአምላካህ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሕዝብ ነህና፥ የፍየሉን ጠቦት በእናቱ ወተት አትቀቅል።