እንዳይረክሱም ወደ ሞተ ሰው አይግቡ፤ ነገር ግን ለአባት፥ ወይም ለእናት፥ ወይም ለወንድ ልጅ፥ ወይም ለሴት ልጅ፥ ወይም ለወንድም፥ ወይም ላልተዳረች እኅት ይርከሱ።
ዘሌዋውያን 21:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፥ “ከወገናቸው በሞተ ሰው ራሳቸውን እንዳያረክሱ ለካህናቱ ለአሮን ልጆች ንገራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለካህናቱ ለአሮን ልጆች ንገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ማንኛውም ሰው ከዘመዶቹ መካከል ስለ ሞተው ሰው ራሱን አያርክስ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለካህናቱ ለአሮን ልጆች እንዲህ ብለህ ለእነርሱ ተናገር፦ ማንም ሰው ከሕዝቡ መካከል ስለ ሞተው ራሱን አያርክስ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከሕዝቡ መካከል የሞተውን ሰው አስከሬን በመንካት ስለ ሞተ ሰው ማናቸውም ራሳቸውን እንዳያረክሱ የአሮን ተወላጆች ለሆኑ ካህናት ንገራቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ለካህናቱ ለአሮን ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው አለው፦ ማንም ሰው ከሕዝቡ ስለ ሞተው፥ |
እንዳይረክሱም ወደ ሞተ ሰው አይግቡ፤ ነገር ግን ለአባት፥ ወይም ለእናት፥ ወይም ለወንድ ልጅ፥ ወይም ለሴት ልጅ፥ ወይም ለወንድም፥ ወይም ላልተዳረች እኅት ይርከሱ።
ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! አድምጡ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ! ልብ አድርጉ፤ ለሚመለከት ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው።
“የእስራኤል ልጆች ለምጻሙን ሁሉ ፈሳሽ ነገርም ያለበትን ሁሉ በሰውነቱ የረከሰውን ሁሉ ከሰፈሩ እንዲያወጡ እዘዛቸው፤