ላሜሕም ለሚስቶቹ ለዓዳና ለሴላ አላቸው፥ “እናንት የላሜሕ ሚስቶች ቃሌን ስሙ፤ ነገሬንም አድምጡ፤ እኔ ጐልማሳውን ስለ መቍሰሌ፤ ብላቴናውንም ስለ መወጋቴ ገድየዋለሁና፤
ዘሌዋውያን 19:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አትበቀል፤ በሕዝብህም ልጆች ቂም አትያዝ፤ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ወገንህን አትበቀል፤ ወይም በመካከልህ ከሚኖር በማንኛውም ሰው ላይ ቂም አትያዝ፤ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አትበቀል፥ በሕዝብህም ልጆች ላይ ቂም አትያዝ፥ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ ጌታ ነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መበቀል አትፈልግ፤ በወገንህ በማንም ላይ ቂም አትያዝ፤ ነገር ግን ጐረቤትህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አትበቀልም፥ በሕዝብህም ልጆች ቂም አትያዝ፥ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
ላሜሕም ለሚስቶቹ ለዓዳና ለሴላ አላቸው፥ “እናንት የላሜሕ ሚስቶች ቃሌን ስሙ፤ ነገሬንም አድምጡ፤ እኔ ጐልማሳውን ስለ መቍሰሌ፤ ብላቴናውንም ስለ መወጋቴ ገድየዋለሁና፤
አቤሴሎምም አምኖንን ክፉም ሆነ መልካም አልተናገረውም። እኅቱን ትዕማርን ስላስነወራት አቤሴሎም አምኖንን ጠልቶታልና።
አቤሴሎምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደረገ፤ አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፥ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አምኖንን ግደሉ ባልኋችሁ ጊዜ ግደሉት። አትፍሩም፤ ያዘዝኋችሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘዛቸው።
እናንተ በግብፅ ምድር እንግዶች ነበራችሁና፤ ወደ እናንተ የመጣ እንግዳ እንደ ሀገር ልጅ ይሁንላችሁ፤ እርሱን እንደ ራሳችሁ ውደዱት፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።
“እርስ በርሳችሁ ቷደዱ ዘንድ፥ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እንዲሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።
ወንድሞቻችን፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ቍጣን አሳልፏት፥ “እኔ እበቀላለሁ፤ እኔ ብድራትን እከፍላለሁ ይላል እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአልና።
አንተ ሥራህን ታሳምር ዘንድ የእግዚአብሔር መልእክተኞች ናቸውና። ክፉ ብታደርግ ግን ፍራ፤ ሰይፍ የታጠቁም ለከንቱ አይደለም፤ ክፉ አድራጊዎችን ለመቅጣት የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና።
በኦሪት እንዲህ ብሎአልና፥ “አታመንዝር፤ አትግደል፤ አትስረቅ፤ በሐሰት አትመስክር፥ አትመኝ፤” ደግሞ ሌላ ትእዛዝ አለ፤ ነገር ግን የሁሉም ራስ “ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚለው ነው።
ጣዖት ማምለክ፥ ሥራይ ማድረግ፥ መጣላት፥ ኵራት፥ የምንዝር ጌጥ፥ ቅናት፥ ቍጣ፥ ጥርጥር፥ ፉክክር፥ ምቀኝነት፥ መጋደል፥ ስካር ይህንም የመሰለ ሁሉ ነው።
በፍርድ ቀን እበቀላቸዋለሁ፤ እግራቸው በሚሰናከልበት ጊዜ፥ የጥፋታቸው ቀን ቀርቦአልና፥ የተዘጋጀላችሁም ፈጥኖ ይደርስባችኋልና።
“እኔ እበቀላለሁ፤ እኔም ብድራትን እመልሳለሁ፥” ያለውን እናውቀዋለንና፤ ዳግመኛም “እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል።”