Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 13:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በኦ​ሪት እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “አታ​መ​ን​ዝር፤ አት​ግ​ደል፤ አት​ስ​ረቅ፤ በሐ​ሰት አት​መ​ስ​ክር፥ አት​መኝ፤” ደግሞ ሌላ ትእ​ዛዝ አለ፤ ነገር ግን የሁ​ሉም ራስ “ ባል​ን​ጀ​ራ​ህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚ​ለው ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “አታመንዝር”፣ “አትግደል”፣ “አትስረቅ”፣ “አትመኝ” የሚሉትና ሌሎችም ትእዛዞች ቢኖሩም፣ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ” በሚለው በዚህ በአንድ ሕግ ተጠቃልለዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 “አታመንዝር፤ አትግደል፤ አትስረቅ፤ አትመኝ፤” የሚለው እና ሌላም ትእዛዝ ቢኖር፤ በዚህ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤” በሚለው ቃል ተጠቅልሎአል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “አታመንዝር፤ አትግደል፤ አትስረቅ፤ የሌላ ሰው የሆነውን ማናቸውንም ነገር አትመኝ” የሚሉት ትእዛዞችና ሌሎችም ትእዛዞች ሁሉ “ሰውን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ” በሚለው በአንዱ ትእዛዝ ተጠቃለው ይገኛሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በውሸት አትመስክር፥ አትመኝ የሚለው ከሌላይቱ ትእዛዝ ሁሉ ጋር በዚህ፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ በሚለው ቃል ተጠቅልሎአል።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 13:9
13 Referencias Cruzadas  

ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም ‘ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ፤’ የምትለው ናት።


እር​ሱም መልሶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክ​ህን በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹም ሰው​ነ​ትህ፥ በፍ​ጹም ኀይ​ልህ፥ በፍ​ጹም ዐሳ​ብህ ውደ​ደው፤ ባል​ን​ጀ​ራ​ህ​ንም እንደ ራስህ ውደድ ይላል” አለው።


ሁለተኛይቱም ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤’ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም።”


አት​በ​ቀል፤ በሕ​ዝ​ብ​ህም ልጆች ቂም አት​ያዝ፤ ነገር ግን ባል​ን​ጀ​ራ​ህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝና።


ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እና​ን​ተስ ለነ​ጻ​ነት ተጠ​ር​ታ​ች​ኋል፤ ነገር ግን በሥ​ጋ​ችሁ ፈቃድ ለነ​ጻ​ነ​ታ​ችሁ ምክ​ን​ያት አታ​ድ​ር​ጉ​ላት፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም በፍ​ቅር ተገዙ።


እና​ንተ በግ​ብፅ ምድር እን​ግ​ዶች ነበ​ራ​ች​ሁና፤ ወደ እና​ንተ የመጣ እን​ግዳ እንደ ሀገር ልጅ ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ እር​ሱን እንደ ራሳ​ችሁ ውደ​ዱት፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።


ትእ​ዛ​ዛ​ቱን አንተ ራስህ ታው​ቃ​ለህ፤ ‘አት​ግ​ደል፤ አታ​መ​ን​ዝር፤ አት​ስ​ረቅ፤ በሐ​ሰት አት​መ​ስ​ክር፤ አባ​ት​ህ​ንና እና​ት​ህ​ንም አክ​ብር።’


ትእዛዛትን ታውቃለህ፤ አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አታታልል፥ አባትህንና እናትህን አክብር፤” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios