በምድርም ሁሉ ዐመፅ ነበረ፥ ከእስራኤልም ልጆች ፊት እግዚአብሔር ያሳደዳቸው የአሕዛብን ርኵሰት ሁሉ ያደርጉ ነበር።
ዘሌዋውያን 18:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ከእናንተ በፊት የነበሩ ሰዎች የሠሩትን ጸያፍ የሆነውን ወግ ሁሉ እንዳትሠሩ፥ በእርሱም እንዳትረክሱ ሥርዐቴን ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትእዛዜን ጠብቁ፤ ከእናንተ በፊት በምድሪቱ የኖሩ ሰዎች ካደረጓቸው አስጸያፊ ድርጊቶች አንዱንም አትፈጽሙ፤ በእነዚህም ራሳችሁን አታርክሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ከእናንተ በፊት በምድሪቱ ላይ የተደረገውን ጸያፍ ወግ ሁሉ ፈጽሞ እንዳታደርጉ፥ በእርሱም ራሳችሁን ፈጽሞ እንዳትረክሱ ሥርዓቴን ጠብቁ፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዝ ሁሉ ፈጽሙ፤ ከእናንተ በፊት በምድሪቱ ይፈጽሙት የነበረውን የረከሰ ልማድ አትከተሉ፤ ከእነዚህ አሳፋሪ ተግባሮች አንዱንም በመፈጸም ራሳችሁን አታርክሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ከእናንተ በፊት የነበሩ ሰዎች የሠሩትን ጸያፍ የሆነውን ወግ ሁሉ እንዳትሠሩ፥ በእርሱም እንዳትረክሱ ሥርዓቴን ጠብቁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። |
በምድርም ሁሉ ዐመፅ ነበረ፥ ከእስራኤልም ልጆች ፊት እግዚአብሔር ያሳደዳቸው የአሕዛብን ርኵሰት ሁሉ ያደርጉ ነበር።
ይህም ከተፈጸመ በኋላ የሕዝቡ አለቆች ወደ እኔ ቀርበው፥ “የእስራኤል ሕዝብ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ እንደ ከነዓናውያን፥ እንደ ኬጤዎናውያን፥ እንደ ፌርዜዎናውያን፦ እንደ ኢያቡሴዎናውያን፥ እንደ አሞናውያን፥ እንደ ሞዓባውያን፥ እንደ ግብፃውያንና እንደ አሞራውያን ርኵሰት ያደርጋሉ እንጂ ከምድር አሕዛብ አልተለዩም፤
ቢያረክሱአት እንዳይሞቱ፥ ስለ እርስዋም ኀጢአትን እንዳይሸከሙ፥ ሕግን ይጠብቁ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝና።
አምላኮቻቸውንም እንዳትሻ፥ አሕዛብም ለአምላኮቻቸው እንደሚያደርጉ እኔም አደርጋለሁ እንዳትል ራስህን ጠብቅ።
ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እንዲሁ አታድርግ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአምላኮቻቸው በእሳት ስለሚያቃጥሉ አሕዛብ ለአምላኮቻቸው የሚያደርጉትን ርኩስ ነገር እግዚአብሔር ይጠላልና።
እኔም ዕቅብቴን ይዤ በመለያያዋ ቈራረጥኋት፤ በእስራኤልም ዘንድ እንደዚህ ያለ ስንፍና ስለ ሠሩ ወደ እስራኤል ርስት አውራጃ ሁሉ ሰደድሁ።