እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ፤ ዞርሁ በድንኳኑም መሥዋዕትን ሠዋሁ፥ እልልም አልሁለት እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፥ እዘምርለትማለሁ።
ዘሌዋውያን 15:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መኝታውንም የሚነካ ሰው ሁሉ ልብሱን ይጠብ፤ በውኃም ሰውነቱን ይታጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐልጋውን የነካ ማንኛውም ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መኝታውንም የሚነካ ማንም ሰው ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አልጋውን የሚነካም ሆነ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መኝታውንም የሚነካ ሁሉ ልብሱን ይጠብ፥ በውኃም ይታጠብ፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው። |
እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ፤ ዞርሁ በድንኳኑም መሥዋዕትን ሠዋሁ፥ እልልም አልሁለት እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፥ እዘምርለትማለሁ።
ይህም ነገር በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ጆሮ ተሰማ፥ “እስክትሞቱ ድረስ ይህ በደል በእውነት አይሰረይላችሁም” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ፤ እናንተም ከርኵሰታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ፤ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አነጻችኋለሁ።
ከእነርሱም በድናቸው በምንም ላይ ቢወድቅ እርሱ ርኩስ ነው፤ የዕንጨት ዕቃ ወይም ልብስ ወይም ቍርበት ወይም ከረጢት ቢሆን የሚሠራበት ዕቃ ሁሉ እርሱን በውኃ ውስጥ ይንከሩት፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።
ካህኑም በሰባተኛው ቀን ቈረቈሩን ያያል፤ እነሆም፥ ከተላጨ በኋላ ቈረቈሩ በቆዳው ላይ ባይሰፋ፥ መልኩም ወደ ቆዳው ባይጠልቅ፥ ካህኑ፦ ‘ንጹሕ ነው’ ይለዋል፤ ልብሱን አጥቦ ንጹሕ ይሆናል።
ደግሞ በሰባተኛው ቀን ካህኑ ያየዋል፤ እነሆም፥ ያች ደዌ ብትከስም፥ በቆዳውም ላይ ባትሰፋ፥ ካህኑ፦ ‘ንጹሕ ነው’ ይለዋል፤ ምልክት ነውና፥ ልብሱንም አጥቦ ንጹሕ ይሆናል።
ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው በተቀመጠበት ነገር ላይ የሚቀመጥበት ሰው ልብሱን ይጠብ፤ በውኃም ይታጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።
ለመለቀቅ የሚሆነውን ፍየል የወሰደ ሰው ልብሱን ያጥባል፤ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገባል።
የሞተውን ወይም አውሬ የሰበረውን የሚበላ ሰው ሁሉ፥ የሀገር ልጅ ወይም እንግዳ ቢሆን፥ ልብሱን ያጥባል፤ በውኃም ይታጠባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።
የጊደሪቱንም አመድ ያከማቸው ሰው ልብሱን ያጥባል፤ ገላውንም ይታጠባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ይህም ለእስራኤል ልጆች በመካከላቸውም ለሚኖር መጻተኛ ለዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል።
እንግዲህ ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን፥ ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ።
ነውር የሌለው ሆኖ፥ በዘለዓለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እናመልከው ዘንድ ሕሊናችንን ከሞት ሥራ እንዴት ይልቅ ያነጻ ይሆን?
ይህስ ባይሆን ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ በሞተ ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ፥ ራሱን በመሠዋት ኀጢአትን ይሽራት ዘንድ አንድ ጊዜ ተገለጠ።
ሳኦልም፥ “አንድ ነገር ሆኖ ይሆናል፤ ምንአልባትም ንጹሕ አይደለም ይሆናል፤ በእውነትም ንጹሕ አይደለም” ብሎ አስቦአልና በዚያ ቀን ምንም አልተናገረም።