ዘሌዋውያን 10:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመሥዋዕቱን ወርችና ፍርምባ በእግዚአብሔር ፊት ከሚቀርበው መሥዋዕት የእሳት ቍርባን ከሆነው ስብ ጋር ያመጣሉ፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘ ለአንተ፥ ከአንተ ጋርም ለወንዶችና ሴቶች ልጆችህ የዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀረበውን ወርችና የተወዘወዘውን ፍርምባ በእግዚአብሔር ፊት የመወዝወዝ መሥዋዕት ሆኖ በእሳት ከቀረበው ሥብ ጋራ ይምጣ። ይህም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ለአንተና ለልጆችህ ለዘላለም የተመደበ ድርሻ ይሆናል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚነሣውን ወርች የሚወዘወዘውንም ፍርምባ፥ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ከሆነው ስብ ጋር ለመወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት እንዲወዘወዝ ያመጣሉ፤ ጌታ እንዳዘዘ ለአንተ ከአንተ ጋርም ላሉት ለልጆችህ የዘለዓለም ድርሻ ይሆናል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስቡ ለእግዚአብሔር የምግብ መባ ሆኖ በሚቀርብበት ጊዜ ወርቹንና ፍርምባውን ያመጣሉ፤ ይህም ሁሉ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ለአንተና ለልጆችህ ለዘለዓለም የተመደበ ድርሻ ይሆናል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚነሣውን ወርች የሚወዘወዘውንም ፍርምባ በእግዚአብሔር ፊት ለመወዝወዝ ቍርባን እንዲወዘውዙ የእሳት ቍርባን ከሆነው ስብ ጋር ያመጣሉ፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘ ለአንተ ከአንተ ጋርም ለልጆችህ የዘላለም ሥርዓት ይሆናል። |
አብርሃምም በግንባሩ ወደቀ፤ ሳቀም፤ በልቡም እንዲህ ብሎ አሰበ፥ “የመቶ ዓመት ሰው ስሆን በውኑ እኔ ልጅ እወልዳለሁን? ዘጠና ዓመት የሆናትም ሣራ ትወልዳለችን?”
በውስጥዋ የምትኖርባትን ይህችን ምድር፥ የከነዓንን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ይገዙአት ዘንድ ለዘርህ እሰጣለሁ፤ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”
ከሚካኑበትም አውራ በግ የተወሰደ ለአሮንና ለልጆቹ ወግ የሚሆን ለመሥዋዕት የተለየውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ።
ይህም የተለየ ቍርባን ነውና ከእስራኤልልጆች ዘንድ ለዘለዓለም የአሮንና የልጆቹ ሕግ ይሁን፤ የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡት የደኅንነት መሥዋዕታቸው የተለየ ቍርባን ይሆናል፤ ለእግዚአብሔር የተለየ ቍርባን ይሆናል።
ፍርምባውንና የቀኝ ወርቹን ከእስራኤል ልጆች ከደኅንነት መሥዋዕታቸው ወስጄአለሁ፤ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ለዘለዓለም ሕግ እንዲሆን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ሰጥቼአቸዋለሁ።”