ዘሌዋውያን 1:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመሠዊያውም አጠገብ በመስዕ በኩል በእግዚአብሔር ፊት ያርዱታል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚቀርበውን መሥዋዕት ከመሠዊያው በስተሰሜን በኩል በእግዚአብሔር ፊት ይረደው፤ ካህናቱ የአሮን ልጆችም ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ሁሉ ይርጩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመሠዊያውም አጠገብ በስተ ሰሜን በኩል በጌታ ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱንም ከመሠዊያው በስተ ሰሜን በኩል በእግዚአብሔር ፊት ይረደው፤ የአሮን ዘር የሆኑ ካህናትም ደሙን ወስደው በመሠዊያው ጐኖች ሁሉ ላይ ይርጩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመሠዊያውም አጠገብ በሰሜን ወገን በእግዚአብሔር ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል። |
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ገበታውን በምስክሩ ድንኳን ውስጥ፥ ከመጋረጃው ውጭ በድንኳኑ በመስዕ በኩል አኖረው፤
እንዲህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያቀርቡበት ዘንድ፥ ደሙንም ይረጩበት ዘንድ በሚሠሩበት ቀን የመሠዊያው ሕግ ይህ ነው።
እርሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ዐይንህን ወደ ሰሜን መንገድ አንሣ” አለኝ። ዐይኔንም ወደ ሰሜን መንገድ አነሣሁ፤ እነሆም በመሠዊያው በር በሰሜን በኩል በመግቢያው ይህ የቅንዓት ምስል ነበረ። ከዚያም ወደ ምሥራቅ ያስገባል።
በሬውንም በእግዚአብሔር ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን ያቀርባሉ፤ ደሙንም በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።
የኀጢአትን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያርዱበት በተቀደሰው ስፍራ ጠቦቱን ያርዱታል፤ የበደሉ መሥዋዕት ለካህኑ እንደሚሆን፥ እንዲሁ የኀጢአቱ መሥዋዕት ነውና፤ ቅዱሰ ቅዱሳን ነው።
እጁንም በኀጢአት መሥዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፤ ለሚቃጠልም መሥዋዕት እንስሳትን በሚያርዱበት ስፍራ የኀጢአት መሥዋዕት ፍየልዋን ያርዳታል።
“አሮንንና ልጆቹን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ የኀጢአት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የኀጢአቱ መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት ይታረዳል፤ እርሱም ቅዱሰ ቅዱሳን ነው።
የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያርዱበት ስፍራ የበደሉን መሥዋዕት በግ በዚያ ያርዱታል፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።