ሰቈቃወ 5:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባሪያዎች ሠልጥነውብናል፤ ከእጃቸውም የሚታደገን የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሮች ሠልጥነውብናል፤ ከእጃቸው ነጻ የሚያወጣን ማንም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባርያዎች ሠልጥነውብናል፥ ከእጃቸው የሚታደገን የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባሪያዎች ይገዙናል፤ ከእጃቸውም ሊያድነን የሚችል የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዎች ሠልጥነውብናል፥ ከእጃቸው የሚታደገን የለም። |
ሖሮናዊውም ሰንባላጥ፥ አገልጋዩም አሞናዊው ጦቢያ፥ ዓረባዊውም ጌሳም በሰሙ ጊዜ በንቀት ሳቁብን፤ ቀላል አድርገውንም ወደ እኛ መጡና፥ “ይህ የምታደርጉት ነገር ምንድን ነው? በውኑ በንጉሡ ላይ ትሸፍቱ ዘንድ ትወድዳላችሁን?” አሉ።
ከእኔ አስቀድመው የነበሩት አለቆች ግን በሕዝቡ ላይ አክብደው ነበር፤ ስለ እንጀራውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወስዱ ነበር፤ ሎሌዎቻቸውም ደግሞ በሕዝቡ ላይ ይሰለጥኑ ነበር። እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈራሁ እንዲህ አላደረግሁም።
ልጆቻቸው ከደኅንነት ርቀዋል፥ በበርም ውስጥ ይቀጠቅጡአቸዋል፤ መከራም ያጸኑባቸዋል፥ የሚታደጋቸውም የለም።
ከእንግዲህ ወዲህ በምድር ላይ ለሚኖሩ አልራራም፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እነሆም፥ ሰውን ሁሉ በባልንጀራውና በንጉሡ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፣ ምድሪቱም ይመታሉ፥ ከእጃቸውም አላድናቸውም።