አለዚያም ብላቴናው ከእኛ ጋር ከሌለ እኔ ወደ አባታችን እንዴት እሄዳለሁ? አባታችንን የሚያገኘውን መከራ እንዳላይ።”
ሰቈቃወ 3:51 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ከተማዬ ቈነጃጅት ሁሉ ዐይኔ ነፍሴን አሳዘነች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በከተማዬ ባሉት ሴቶች ሁሉ ላይ የደረሰውን ማየቴ፣ ነፍሴን አስጨነቃት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ከተማዬ ቈነጃጅት ሁሉ ዓይኔ ነፍሴን አሳዘነች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከተማዬ ውስጥ ባሉት ወጣት ሴቶች ላይ የደረሰውን ክፉ ዕድል በማየቴ የመረረ ሐዘን ደረሰብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ከተማዬ ቈነጃጅት ሁሉ ዓይኔ ነፍሴን አሳዘነች። |
አለዚያም ብላቴናው ከእኛ ጋር ከሌለ እኔ ወደ አባታችን እንዴት እሄዳለሁ? አባታችንን የሚያገኘውን መከራ እንዳላይ።”
ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በመዓት እጐበኛቸዋለሁ፤ ጐበዛዝቶቻቸው በሰይፍ ይሞታሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በራብ ይሞታሉ፤
ትንቢት የሚናገሩላቸውም ሰዎች ከራብና ከሰይፍ የተነሣ በኢየሩሳሌም መንገዶች ይበተናሉ፤ ክፋታቸውንም አፈስስባቸዋለሁና እነርሱንና ሚስቶቻቸውን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም የሚቀብራቸው አይገኝም።
ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ በሰይፍ የሞቱ አሉ፤ ወደ ከተማም ብገባ፥ እነሆ በራብ የከሱ አሉ፤ ነቢዩና ካህኑ ወደማያውቋት ሀገር ሄደዋልና።”
የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውንም ሥጋ አበላቸዋለሁ፤ ሁሉም እያንዳንዳቸው ጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውን የሚሹት በሚያስጨንቋቸው ጭንቀትና መከበብ የባልንጀሮቻቸውን ሥጋ ይበላሉ።
ጻዴ። ቃሉን አማርሬአለሁና እግዚአብሔር ጻድቅ ነው። እናንተ አሕዛብ ሁሉ እባካችሁ ስሙ፤ መከራዬንም ተመልከቱ፤ ደናግሎችና ጐልማሶች ተማርከው ሄደዋልና።
ካፍ። ሕፃኑና ጡት የሚጠባው በከተማዪቱ ጎዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዐይኔ በእንባ ደከመች፤ ልቤም ታወከ፤ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ መከራ ክብሬ በምድር ላይ ተዋረደ።
ሣን። ብላቴናውና ሽማግሌው በመንገዶች ላይ ተጋደሙ፤ ደናግሎችና ጐልማሶች ተማርከዋል፤ በሰይፍም ወድቀዋል፤ በረኃብ ገደልሃቸው፤ በቍጣህም ቀን ሳትራራ አረድሃቸው።