ሰቈቃወ 1:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሣን። እኔ እንደማለቅስ ሰምተዋል፤ የሚያጽናናኝ የለም፤ ጠላቶች ሁሉ መከራዬን ሰምተዋል፤ አንተ አድርገኸዋልና ደስ አላቸው፤ ስለ እርሱ የተናገርኸውን ቃል ታመጣለህ፤ እነርሱም እንደ እኔ ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሰዎች የሥቃይ ልቅሶዬን ሰሙ፤ የሚያጽናናኝ ግን ማንም የለም፤ ጠላቶቼ ሁሉ ጭንቀቴን ሰሙ፤ አንተ ባደረግኸውም ደስ አላቸው፤ አቤቱ የተናገርሃት ቀን ትምጣ፤ እነርሱም እንደ እኔ ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳን። እኔ እየጮኽሁ እንደማለቅስ ሰምተዋል፥ የሚያጽናናኝ የለም፥ ጠላቶቼ ሁሉ ስለ መከራዬ ሰምተዋል፥ አንተ አድርገኸዋልና ደስ አላቸው፥ ስለ እርሱ የተናገርኸውን ቀን ታመጣለህ እነርሱም እንደ እኔ ይሆናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ጠላቶቼ ሁሉ ማንም የሚያጽናናኝ ሰው በሌለበት እንዴት እንደምቃትትና እንደምቸገር ሰሙ፤ አንተ ያደረግኸው መሆኑንም ዐውቀው ተደሰቱ፤ በእነርሱ ላይ ልታመጣባቸው የወሰንከውን ቀን አምጣና እንደ እኔ ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳን። እኔ እየጮኽሁ እንደማለቅስ ሰምተዋል፥ የሚያጽናናኝ የለም፥ ጠላቶቼ ሁሉ ስለ መከራዬ ሰምተዋል፥ አንተ አድርገኸዋልና ደስ አላቸው፥ ስለእርሱ የተናገርኸውን ቀን ታመጣለህ እነርሱም እንደ እኔ ይሆናሉ። |
ስለዚህ የሚበሉህ ሁሉ ይበላሉ፤ የሚማርኩህም ሁላቸው ይማረካሉ፤ የዘረፉህም ይዘረፋሉ፤ የሚማርኩህንም ሁሉ ለመማረክ አሳልፌ እሰጣለሁ።
እስራኤል ለአንተ መሳቂያ አልሆነምን? ወይስ በሌቦች መካከል ተገኝቶአልን? ስለ እርሱ በተናገርህ ጊዜ ራስህን ትነቀንቃለህ።
“ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ ሆይ! ደስ ብሎአችኋልና፥ ሐሤትንም አድርጋችኋልና፥ በመስክ ላይም እንዳለች ጊደር ሆናችሁ ተቀናጥታችኋልና፥ እንደ ብርቱዎችም በሬዎች ቷጋላችሁና፤
እጆችዋ ደክመዋልና ክበቡአት፤ ግንቧ ወድቋል፤ ቅጥርዋም ፈርሶአል፤ የእግዚአብሔርም በቀል ነውና ተበቀሏት፤ እንደ ሠራችውም ሥሩባት።
“ቀስትን የሚገትሩ ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው፤ በዙሪያዋ ስፈሩባት፤ ከእርስዋም ሰዎች አንድ አያምልጥ፤ የእስራኤልን ቅዱስ እግዚአብሔርን ተቃውማለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፤ እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት።
ትዕቢተኛ ሆይ! አንቺን የሚበቀሉበት ጊዜ፥ ቀንሽ ደርሶአልና እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
በጽዮን በዐይናችሁ ፊት ስለ ሠሩት ክፋታቸው ሁሉ በባቢሎንና በከለዳውያን ምድር የሚኖሩትን ሁሉ እበቀላለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ዔ። የሚያጽናናኝ፥ ነፍሴንም የሚመልሳት ከእኔ ርቆአልና ዐይኔ ውኃ ያፈስሳል። ጠላት በርትቶአልና ልጆች ጠፍተዋል።
ቤት። በሌሊት እጅግ ታለቅሳለች፤ እንባዋም በጉንጭዋ ላይ አለ፤ ከሚያፈቅሩአት ሁሉ የሚያጽናናት የለም፤ ወዳጆችዋም ሁሉ ወነጀሉአት፤ ጠላቶችም ሆኑአት።
ታው። ልቅሶዬ እጅግ ነውና፥ ልቤም ደክሞአልና፥ ክፋታቸው ሁሉ ወደ ፊትህ ይድረስ፥ ስለ ኀጢአቴ ሁሉ እኔን እንደ ቃረምኸኝ እነርሱን ቃርማቸው።
ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓል የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ፤ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል፤ ካህናቷም ያለቅሳሉ፤ ደናግሎችዋም ተማረኩ፤ እርስዋም በምሬት አለች።
ሔት። ኢየሩሳሌም እጅግ ኀጢአት ሠርታለች፤ ስለዚህ ረክሳለች፤ በተጨነቀችበት ቦታ ያከብሩአት የነበሩ ሁሉ ውርደቷን አይተዋልና አቃለሉአት፤ እርስዋም እየጮኸች ታለቅሳለች፤ ወደ ኋላዋም ዘወር አለች።
ሳምኬት። መንገድ ዐላፊዎች ሁሉ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻል፦ “በውኑ የምድር ሁሉ ደስታ፥ አክሊልና ክብር የሚሉአት ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ፥ በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍዋጫሉ፤ ራሳቸውንም ይነቀንቃሉ።
ዔ። ጠላቶችሽ ሁሉ አፋቸውን አላቀቁብሽ፤ እያፍዋጩና ጥርሳቸውን እያፋጩ፥ “ውጠናታል፤ ነገር ግን ተስፋ ያደረግናት ቀን ይህች ናት፤ አግኝተናታል አይተናትማል” ይላሉ።
“የሰው ልጅ ሆይ፥ ጢሮስ በኢየሩሳሌም ላይ፦ እሰይ፥ ተሰበረች፥ ጠፋችም፥ ሕዝቧም ወደ እርስዋ ተመለሱ፤ ሞልታ የነበረች አለቀች ብላለችና፤