ሰቈቃወ 1:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤት። በሌሊት እጅግ ታለቅሳለች፤ እንባዋም በጉንጭዋ ላይ አለ፤ ከሚያፈቅሩአት ሁሉ የሚያጽናናት የለም፤ ወዳጆችዋም ሁሉ ወነጀሉአት፤ ጠላቶችም ሆኑአት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሌሊት አምርራ ታለቅሳለች፤ እንባዋ በጕንጮቿ ላይ ይወርዳል፤ ከወዳጆቿ ሁሉ መካከል፣ የሚያጽናናት ማንም የለም፤ ባልንጀሮቿ ሁሉ ከድተዋታል፤ ጠላቶቿም ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤት። በሌሊት እጅግ ታላቅሳለች፥ እንባዋም በጉንጭዋ ላይ አለ፥ ከውሽሞችዋ ሁሉ የሚያጽናናት የለም፥ ወዳጆችዋ ሁሉ ወነጀሉአት ጠላቶችም ሆኑአት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሌሊት እጅግ ታለቅሳለች፤ እንባዋ በጒንጮችዋ ላይ ይወርዳል፤ ከአፍቃሪዎችዋ ሁሉ እርስዋን የሚያጽናና አንድ እንኳ የለም፤ ወዳጆችዋ የነበሩ ሁሉ ከድተዋታል፤ በጠላትነትም ተነሥተውባታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤት። በሌሊት እጅግ ታላቅሳለች፥ እንባዋም በጉንጭዋ ላይ አለ፥ ከውሽሞችዋ ሁሉ የሚያጽናናት የለም፥ ወዳጆችዋ ሁሉ ወነጀሉአት ጠላቶችም ሆኑአት። |
ድሃ ወንድሙንም የሚጠላ ሰው ሁሉ፥ ከወንድምነቱ የራቀ ነው። በጎ ዕውቀትም ወደሚያውቋት ትቀርባለች። ብልህ ሰውም ያገኛታል። ብዙ ክፋትን የሚሠራ ክፋትን ይፈጽማል፥ ስቅጥጥ የሚያደርግ ነገርን የሚናገርም አይድንም።
ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔርም መንጋ ተሰብሮአልና ዐይኔ ታነባለች፤ እንባንም ታፈስሳለች።
እግርሽን ከሰንከልካላ መንገድ፥ ጕሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ፤ እርስዋ ግን፥ “እጨክናለሁ፤ እንግዶችንም ወድጄአለሁ” ብላ ተከተለቻቸው።
“ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ ከእርሱም ዘንድ ሄዳ ሌላ ወንድ ብታገባ፥ በውኑ ደግሞ ወደ እርሱ ትመለሳለችን? ያች ሴት እጅግ የረከሰች አይደለችምን? አንቺም ከብዙ እረኞች ጋር አመንዝረሻል፤ ወደ እኔም ትመለሻለሽን? ይላል እግዚአብሔር።
ወዳጆችህ ሁሉ ረስተውሃል፤ አይፈልጉህምም፤ በደልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢአትህም ስለ በዛ፥ በጠላት ማቍሰልና በጨካኝ ቅጣት አቍስዬሃለሁና።
አንቺስ ምን ታደርጊያለሽ? ቀይ በለበስሽ ጊዜ፥ በወርቅ አንባርም ባጌጥሽ ጊዜ፥ ዐይንሽንም በኵል በተኳልሽ ጊዜ፥ በከንቱ ታጌጫለሽ፤ ፍቅረኞችሽ አቃለሉሽ፥ ነፍስሽን ይሹአታል።
ቆፍ። ወዳጆችን ጠራሁ፤ እነርሱም ቸል አሉኝ፤ ካህናቶችና ሽማግሌዎች ሰውነታቸውን ያበረቱ ዘንድ መብል ሲፈልጉ በከተማ ውስጥ ሳያገኙ አለቁ።
ሣን። እኔ እንደማለቅስ ሰምተዋል፤ የሚያጽናናኝ የለም፤ ጠላቶች ሁሉ መከራዬን ሰምተዋል፤ አንተ አድርገኸዋልና ደስ አላቸው፤ ስለ እርሱ የተናገርኸውን ቃል ታመጣለህ፤ እነርሱም እንደ እኔ ይሆናሉ።
ጤት። ግዳጅዋ ከእግርዋ በታች ነበረ፤ ፍጻሜዋን አላሰበችም፤ ከባድ ሸክምን ተሸከመች፤ የሚያጽናናትም የለም፤ አቤቱ! ጠላት ከፍ ከፍ ብሎአልና መከራዬን ተመልከት።
ካፍ። ሕፃኑና ጡት የሚጠባው በከተማዪቱ ጎዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዐይኔ በእንባ ደከመች፤ ልቤም ታወከ፤ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ መከራ ክብሬ በምድር ላይ ተዋረደ።
ስለዚህ እነሆ እኔ ከአንቺ ጋር አንድ የሆኑ ውሽሞችሽን በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤ የምትወጃቸውንም ከምትጠያቸው ጋር በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤ ይከቡሻል፤ በእነርሱም ዘንድ ጕስቍልናሽን እገልጥብሻለሁ፤ ሁሉም ኀፍረትሽን ያዩብሻል።
ወዳጆችዋንም ትከተላለች፤ ነገር ግን አትደርስባቸውም፤ ትፈልጋቸውማለች፤ ነገር ግን አታገኛቸውም፤ እርስዋም፥ “ከዛሬ ይልቅ የዚያን ጊዜ ይሻለኝ ነበርና ተመልሼ ወደ ቀደመው ባሌ እሄዳለሁ” ትላለች።