La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 6:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ይዘው በብ​ዛት እንደ አን​በጣ ሆነው ይመ​ጡ​ባ​ቸው ነበር፤ ለእ​ነ​ር​ሱና ለግ​መ​ሎ​ቻ​ቸው ቍጥር አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ያጠ​ፏት ዘንድ ይመጡ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከብቶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው ሲመጡ ልክ የአንበጣ መንጋ ይመስሉ ነበር፤ ሰዎቹንም ሆነ ግመሎቻቸውን ለመቍጠር አዳጋች ሲሆን፣ የሚመጡትም ምድሪቱን ለማጥፋት ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከብቶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው ሲመጡ ልክ የአንበጣ መንጋ ይመስሉ ነበር፤ ሰዎቹንም ሆነ ግመሎቻቸውን ለመቁጠር አዳጋች ሲሆን፥ የሚመጡትም ምድሪቱን ለማጥፋት ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከከብቶቻቸውና ከድንኳኖቻቸው ጋር ሲመጡ ያንበጣ መንጋ ይመስሉ ነበር፤ እነርሱንና ግመሎቻቸውን ለመቊጠር እስከማይቻል ድረስ እጅግ ብዙዎች ነበሩ፤ መጥተውም ምድሪቱን ያጠፉ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንስሶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው በብዛት እንደ አንበጣ ሆነው ይመጡ ነበር፥ ለእነርሱና ለግመሎቻቸውም ቁጥር አልነበራቸውም፥ ምድሪቱንም ያጠፉ ዘንድ ይመጡ ነበር።

Ver Capítulo



መሳፍንት 6:5
13 Referencias Cruzadas  

እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፤ ነገር ግን ውብ ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድን​ኳ​ኖች እንደ ሰሎ​ሞ​ንም መጋ​ረ​ጃ​ዎች።


ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባት አይ​ገ​ኝም፤ ከት​ው​ል​ድም እስከ ትው​ልድ ድረስ ሰው አይ​ኖ​ር​ባ​ትም፤ ዓረ​ባ​ው​ያ​ንም በእ​ርሷ አያ​ል​ፉም፤ እረ​ኞ​ችም በው​ስ​ጥዋ አያ​ር​ፉም።


የግ​መ​ሎች መንጋ ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፤ የም​ድ​ያ​ምና የኤፋ ግመ​ሎች ይሸ​ፍ​ኑ​ሻል፤ ሁሉ ከሳባ ወር​ቅ​ንና ዕጣ​ንን ይዘው ይመ​ጣሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ማዳን ያበ​ሥ​ራሉ።


ሊቈ​ጠሩ የማ​ይ​ችሉ የዱ​ር​ዋን ዛፎች ይቈ​ር​ጣሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከአ​ን​በጣ ይልቅ በዝ​ተ​ዋ​ልና፥ ቍጥ​ርም የላ​ቸ​ው​ምና።


ድን​ኳ​ና​ቸ​ው​ንና በጎ​ቻ​ቸ​ውን ይወ​ስ​ዳሉ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንና ዕቃ​ቸ​ውን ሁሉ፥ ግመ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለራ​ሳ​ቸው ይወ​ስ​ዳሉ፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ሁሉ ጥፋ​ትን ጥሩ​ባ​ቸው።


ግመ​ሎ​ቻ​ቸው ለም​ርኮ ይሆ​ናሉ፤ የእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ብዛት ለጥ​ፋት ይሆ​ናል፤ ጠጕ​ራ​ቸ​ው​ንም በዙ​ሪያ የሚ​ላ​ጩ​ትን ሰዎች ወደ ነፋ​ሳት ሁሉ እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከዳ​ር​ቻ​ቸው ሁሉ ጥፋት አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል በራሱ ምሎ​አል፦ በእ​ው​ነት ሰዎ​ችን እንደ አን​በጣ እሞ​ላ​ብ​ሻ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም እየ​ሮጡ ይወ​ር​ዱ​ብ​ሻል።”


የም​ድ​ር​ህን ፍሬ፥ ድካ​ም​ህ​ንም ሁሉ የማ​ታ​ው​ቀው ሕዝብ ይበ​ላ​ዋል፤ አን​ተም ሁል​ጊዜ የተ​ጨ​ነ​ቅህ፥ የተ​ገ​ፋ​ህም ትሆ​ና​ለህ።


ብዛ​ታ​ቸ​ውም እንደ አን​በጣ የሆነ ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንና አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን የም​ሥ​ራ​ቅም ልጆች ሁሉ በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ሰፍ​ረው ነበር፤ የግ​መ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም ብዛት ቍጥር እን​ደ​ሌ​ለው በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ ነበረ።


ዛብ​ሄ​ልና ስል​ማ​ናም ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር በቀ​ር​ቀር ነበሩ፤ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ መቶ ሃያ ሺህ ሰዎች ወድ​ቀው ነበ​ርና ከም​ሥ​ራቅ ሰዎች ሠራ​ዊት ሁሉ የቀሩ ዐሥራ አም​ስት ሺህ ያህል ሰዎች ነበሩ።


ዛብ​ሄ​ልና ስል​ማ​ናም፥ “ኀይ​ልህ እንደ ጐል​ማሳ ኀይል ነውና አንተ ተነ​ሥ​ተህ ውደ​ቅ​ብን” አሉት። ጌዴ​ዎ​ንም ተነ​ሥቶ ዛብ​ሄ​ል​ንና ስል​ማ​ናን ገደለ፤ በግ​መ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም አን​ገት የነ​በ​ሩ​ትን ሥሉ​ሴ​ዎች ማረከ።


ዳዊ​ትም ሄዶ የአ​ጥ​ቢያ ኮከብ ከሚ​ወ​ጣ​በት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ዳግ​መ​ኛም በማ​ግ​ሥቱ መታ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በግ​መል ተቀ​ም​ጠው ከሸ​ሹት አራት መቶ ጐል​ማ​ሶች በቀር አን​ድም ያመ​ለጠ የለም።