Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 6:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ከም​ድ​ያ​ምም ፊት የተ​ነሣ እስ​ራ​ኤል እጅግ ተቸ​ገሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ምድያማውያን እስራኤላውያንን ችግር ላይ ስለ ጣሏቸው፣ ይረዳቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ምድያማውያን እስራኤላውያንን ችግር ላይ ስለጣሏቸው፥ ይረዳቸው ዘንድ ወደ ጌታ ጮኹ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ በምድያማውያን ምክንያት ችግር ደረሰባቸው፤ እንዲረዳቸውም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ከምድያምም የተነሣ እስራኤል እጅግ ተጠቁ፥ የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 6:6
13 Referencias Cruzadas  

አቤቱ፥ ከን​ፈ​ሮ​ችን ክፈት፥ አፌም ምስ​ጋ​ና​ህን ያወ​ራል።


አቤቱ፥ በመ​ከ​ራዬ ጊዜ አሰ​ብ​ኹህ፤ በጥ​ቂት መከ​ራም ገሠ​ጽ​ኸኝ።


መከ​ር​ህ​ንና እን​ጀ​ራ​ህን ይበ​ላሉ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ህ​ንም ይበ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ በጎ​ች​ህ​ንና ላሞ​ች​ህ​ንም ይበ​ላሉ፤ ወይ​ን​ህ​ንና በለ​ስ​ህ​ንም፥ ዘይ​ት​ህ​ንም ይበ​ላሉ፤ የም​ት​ታ​መ​ና​ቸ​ውን የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ች​ህ​ንም በሰ​ይፍ ያጠ​ፋሉ።”


እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ፥ ፊቴ​ንም እስ​ኪሹ ድረስ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ወደ ስፍ​ራ​ዬም እመ​ለ​ሳ​ለሁ።


ኤዶምያስ፦ እኛ ፈርሰናል፥ ነገር ግን የፈረሰውን መልሰን እንሠራለን ቢል፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነርሱ ይሠራሉ፥ እኔ ግን አፈርሳለሁ፣ በሰዎችም ዘንድ፦ የበደል ዳርቻና እግዚአብሔር ለዘላለም የተቈጣው ሕዝብ ይባላል።


በአ​ንተ መካ​ከል ያለ መጻ​ተኛ በአ​ንተ ላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አንተ ግን ዝቅ ዝቅ ትላ​ለህ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ “አን​ተን አም​ላ​ካ​ች​ንን ትተን በዓ​ሊ​ምን አም​ል​ከ​ና​ልና ኀጢ​አት ሠር​ተ​ናል” ብለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብን​ያ​ማ​ዊ​ውን የጌ​ራን ልጅ ናዖ​ድን ሁለቱ እጆቹ ቀኝ የሆ​ኑ​ለ​ትን ሰው አዳኝ አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ርሱ እጅ ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግ​ሎም እጅ መንሻ ላኩ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል መድ​ኀ​ኒ​ትን አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው። የካ​ሌብ የታ​ናሽ ወን​ድሙ የቄ​ኔዝ ልጅ ጎቶ​ን​ያ​ልም አዳ​ና​ቸው፤ ለእ​ር​ሱም ታዘ​ዙ​ለት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ ዘጠኝ መቶ የብ​ረት ሰረ​ገ​ሎች ነበ​ሩ​ትና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ሃያ ዓመት እጅግ ያስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው ነበር።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በም​ድ​ያም ምክ​ን​ያት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጮኹ ጊዜ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos