መሳፍንት 6:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም መልአክ መጥቶ በኤፍራታ ባለችው ለኤዝሪ አባት ለኢዮአስ በነበረችው ዛፍ በታች ተቀመጠ፤ ልጁም ጌዴዎን ከምድያማውያን ለማሸሽ በወይን መጭመቂያው ውስጥ ስንዴ ይወቃ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር መልአክ ዖፍራ ወደምትባል መንደር መጥቶ፣ በአቢዔዝራዊው በኢዮአስ ዕርሻ ውስጥ በሚገኝ በአንድ የባሉጥ ዛፍ ሥር ተቀመጠ፤ የኢዮአስም ልጅ ጌዴዎን፣ ምድያማውያን እንዳያዩበት ደብቆ በወይን መጭመቂያው ስፍራ ስንዴውን ይወቃ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ መልአክ ዖፍራ ወደምትባል መንደር መጥቶ፥ በአቢዔዝራዊው በኢዮአስ ዕርሻ ውስጥ በሚገኝ በአንድ የባሉጥ ዛፍ ሥር ተቀመጠ፤ የኢዮአስም ልጅ ጌዴዎን፥ ምድያማውያን እንዳያዩት ተደብቆ በወይን መጭመቂያው ስፍራ ስንዴውን ይወቃ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ “ዖፍራ” ተብላ ወደምትጠራው መንደር መጥቶ ከአቢዔዜር ጐሣ የተወለደው የኢዮአስ ንብረት በሆነው የወርካ ዛፍ ሥር ተቀመጠ፤ የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን ምድያማውያን እንዳያዩት ተሸሽጎ በወይን መጭመቂያው ስፍራ የስንዴ ነዶ ይወቃ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም መልአክ መጥቶ በዖፍራ ባለችው ለአቢዔዝራዊው ለኢዮአስ በነበረችው በአድባሩ ዛፍ በታች ተቀመጠ፥ ልጁም ጌዴዎን ከምድያማውያን ለመሸሸግ በወይን መጠመቂያው ውስጥ ስንዴ ይወቃ ነበር። |
ከከፉ ነገር ሁሉ የአዳነኝ መልአክ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፤ ስሜም፥ የአባቶች የአብርሃምና የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ፤ በምድር ላይ ይብዙ፤ የብዙ ብዙም ይሁኑ፤”
ከዚያም ሄደ፤ የሣፋጥንም ልጅ ኤልሳዕን በዐሥራ ሁለት ጥማድ በሬዎች ሲያርስ፥ እርሱም ከዐሥራ ሁለተኛው ጋር ሆኖ አገኘው። ኤልያስም ወደ እርሱ አልፎ መጐናጸፊያውን ጣለበት።
በመልእክተኛም አይደለም፤ በመልአክም አይደለም፤ እርሱ ራሱ ያድናቸዋል እንጂ። እርሱ ይወዳቸዋልና፥ ይራራላቸዋልምና እርሱ ተቤዣቸው፤ ተቀበላቸውም፤ በዘመናቸውም ሁሉ ለዘለዓለም አከበራቸው።
እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎን፥ ስለ ባርቅ፥ ስለ ሶምሶን፥ ስለ ዮፍታሔ፥ ስለ ዳዊት፥ ስለ ሳሙኤልና ስለ ሌሎች ነቢያት እነግራችሁ ዘንድ ጊዜዬ አጭር ነውና።
ዕጣውም ለቀሩት ለምናሴ ልጆች በየወገኖቻቸው፥ ለኢያዜር ልጆች፥ ለቄሌዝ ልጆች፥ ለኢየዚኤል ልጆች፥ ለሴኬም ልጆች፥ ለሱማሪም ልጆች፥ ለኦፌር ልጆች ሆነ፤ ወንዶቹ በየወገኖቻቸው እነዚህ ናቸው።
የእግዚአብሔርም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ እንዲህ አላት፥ “እነሆ፥ አንቺ መካን ነሽ፤ ልጅም አልወለድሽም፤ ነገር ግን ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ።
ሴቲቱም ወደ ባልዋ መጥታ፥ “አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ እጅግ የሚያስደነግጥ ነበረ፤ ከወዴትም እንደ መጣ ጠየቅሁት፥ እርሱም ስሙን አልነገረኝም።
የእግዚአብሔር መልአክ አለ፥ “ሜሮዝን ርገሙ፤ ወደ እግዚአብሔር ርዳታ አልመጡምና፥ በኀያላን መካከል ወደ እርሱ ርዳታ አልመጡምና፥ በቤቶችዋ ያሉትን ሰዎች ፈጽማችሁ ርገሙ።”
እርሱም፥ “እኔ ዛሬ እናንተ እንዳደረጋችሁት ምን አደረግሁ? የኤፍሬም ወይን ቃርሚያ ከአቢዔዜር ወይን መከር አይሻልምን?
ወደ አባቱም ቤት ወደ ኤፍራታ ገባ፤ ሰባ የሆኑትን የይሩበኣልን ልጆች ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ ገደላቸው፤ ትንሹ የይሩበኣል ልጅ ኢዮአታም ግን ተሸሽጎ ነበርና ተረፈ።