እኔም እነሆ፥ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፤ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል።
መሳፍንት 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገሥታት ሆይ፥ ስሙ፤ ጽኑዓን መኳንንትም ሆይ፥ አድምጡ፤ እኔ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፤ እኔ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ ነገሥታት ይህን ስሙ፤ ገዦችም አድምጡ፤ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ደግሜም ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገሥታት ሆይ፥ ስሙ፥ መኳንንት ሆይ፥ አድምጡ፥ እኔ ለጌታ እቀኛለሁ፥ ለእስራኤል አምላክ ለጌታ እዘምራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ነገሥታት ስሙ! እናንተም አለቆች አድምጡ! እኔ ለእግዚአብሔር፥ እዘምራለሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር አዜማለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገሥታት ሆይ፥ ስሙ፥ መኳንንት ሆይ፥ አድምጡ፥ እኔ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፥ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ። |
እኔም እነሆ፥ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፤ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል።
ኤልያስም ሕዝቡን አለ፥ “ከእግዚአብሔር ነቢያት አንድ እኔ ብቻ ቀርቻለሁ፤ የበዓል ነቢያት ግን አራት መቶ ሃምሳ ሰዎች ናቸው። የማምለኪያ ዐፀድ ነቢያትም አራት መቶ ናቸው።
ኤልያስም፥ “ሁሉን ለሚገዛ ለእግዚአብሔር እጅግ ቀንቻለሁ፤ የእስራኤል ልጆች ቃል ኪዳንህን ትተዋልና፥ መሠዊያዎችህንም አፍርሰዋልና፥ ነቢያትህንም በሰይፍ ገድለዋልና፤ እኔም ብቻዬን ቀርቻለሁ ነፍሴንም ሊወስዱአት ይሻሉ” አለ።
እርሱም፥ “ሁሉን ለሚገዛ ለእግዚአብሔር እጅግ ቀንቻለሁ፤ የእስራኤል ልጆች ቃል ኪዳንህን ትተዋልና፥ መሠዊያዎችህንም አፍርሰዋልና፥ ነቢያትህንም በሰይፍ ገድለዋልና፤ እኔም ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ ነፍሴንም ሊወስዱአት ይሻሉ” አለ።
እኔም ንጉሡ አርተሰስታ በወንዝ ማዶ ላሉት ግምጃ ቤቶች ሁሉ ይህን ትእዛዝ ሰጥቻለሁ፦ የሰማይ አምላክ ሕግ ጸሓፊ ካህኑ ዕዝራ ከእናንተ የሚፈልገውን ሁሉ አዘጋጁለት፤
እኔም እነሆ፥ ከዳን ነገድ የሚሆን የአሂሳሚክን ልጅ ኤልያብን ሰጠሁ፤ ያዘዝሁህን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በልባቸው ጥበበኞች ለሆኑት ሁሉ ዕውቅትን ሰጠሁ።