መሳፍንት 5:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተነሺ፥ ዲቦራ ሆይ፦ ተነሺ፤ አእላፍን ከሕዝብ ጋር አስነሺ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ቅኔውንም ተቀኚ፤ ባርቅ ሆይ! በኀይል ተነሣ፤ ዲቦራም ባርቅን አጽኚው፥ የአቢኒሔም ልጅ ባርቅም ሆይ! ምርኮህን ማርክ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ዲቦራ ሆይ፤ ንቂ፤ ንቂ፤ ንቂ፤ ንቂ፤ ቅኔም ተቀኚ፤ የአቢኒኤም ልጅ ባርቅ ሆይ፤ ተነሣ፤ ምርኮኞችህንም ማርከህ ውሰድ’ አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንቂ፥ ንቂ፥ ዲቦራ ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ፥ ቅኔውን ተቀኚ፥ ባራቅ ሆይ፥ ተነሣ፥ የአቢኒኤም ልጅ ሆይ፥ ምርኮህን ማርክ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዲቦራ ሆይ! ንቂ! ንቂ! ንቂ! መዝሙርም ዘምሪ! የአቢኒዔም ልጅ ባራቅ ሆይ! ተነሣ! ምርኮህንም እየመራህ ወደ ፊት ገሥግሥ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንቂ፥ ንቂ፥ ዲቦራ ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ፥ ቅኔውን ተቀኚ፥ ባርቅ ሆይ፥ ተነሣ፥ የአቢኒኤም ልጅ ሆይ፥ ምርኮህን ማርክ። |
አሕዛብም ይዘው ወደ ስፍራቸው ያመጡአቸዋል፤ የእስራኤልም ወገኖች ይካፈሏቸዋል፤ በዚያም ሀገር ይበዛሉ፤ በዚያም ወንዶች ባሮችና ሴቶች ባሮች ይሆናሉ። ማርከው የወሰዷቸውም ለእነርሱ ምርኮኞች ይሆናሉ፤ የገዙአቸውም ይገዙላቸዋል።
ለሚያዋርዱአችሁ ወዮላቸው! እናንተን ግን የሚያዋርዳችሁ የለም፤ የሚወነጅላችሁ እናንተን የሚወነጅል አይደለም፤ ወንጀለኞች ይጠመዳሉ፤ ይያዛሉም፤ ብል እንደበላው ልብስም ያልቃሉ።
ከእግዚአብሔር እጅ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ቁሚ፤ የሚያንገደግድሽን የቍጣውን ጽዋ ጠጥተሻልና፥ ጨልጠሽውማልና።