በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ! በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤ የሸሸውንና ያመለጠውን፦ ምን ሆኖአል? ብለሽ ጠይቂው።
መሳፍንት 11:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልም በሐሴቦንና በመንደሮችዋ፥ በአሮዔርና በመንደሮችዋ፥ በአርኖንም አቅራቢያ ባሉት ከተሞች ሁሉ ሦስት መቶ ዓመት ተቀምጦ በነበረ ጊዜ፥ በዚያ ዘመን ስለ ምን አላዳንሃቸውም ነበር? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤልም በሐሴቦንና በመንደሮቿ፣ በአሮዔርና በመንደሮቿ፣ በአርኖንም አቅራቢያ ባሉት ከተሞች ሁሉ ሦስት መቶ ዓመት ተቀምጦ በነበረበት በዚያ ጊዜ ስለ ምን አልወሰዳችኋቸውም ነበር? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልም በሐሴቦንና በመንደሮችዋ፥ በአሮዔርና በመንደሮችዋ፥ በአርኖንም አቅራቢያ ባሉት ከተሞች ሁሉ ሦስት መቶ ዓመት ተቀምጦ በነበረበት በዚያን ጊዜ ስለምን አልወሰዳችኋቸውም? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሦስት መቶ ዓመት ሙሉ እስራኤል ሐሴቦንና መንደሮችዋን ዓሮዔርንና መንደሮችዋን፥ እንዲሁም በአርኖን ወንዝ ዳርቻ ያሉትን ከተሞች በሙሉ ወርሰው ኖረዋል፤ ታዲያ በነዚህ ዘመናት ሁሉ ስለምን መልሳችሁ አልወሰዳችኋቸውም ነበር? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም በሐሴቦንና በመንደሮችዋ፥ በአሮዔርና በመንደሮችዋ፥ በአርኖንም አቅራቢያ ባሉት ከተሞች ሁሉ ሦስት መቶ ዓመት ተቀምጦ በነበረ ጊዜ፥ በዚያ ዘመን ስለ ምን አልወሰዳችኋቸውም ነበር? |
በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ! በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤ የሸሸውንና ያመለጠውን፦ ምን ሆኖአል? ብለሽ ጠይቂው።
ደግሞም አለ፦ ተነሥታችሁ ሂዱ፤ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ፤ እነሆ፥ አሞሬዎናዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንን፥ ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ እርስዋን ግዛት፤ ውረሳት፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ።
በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔርና በሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ተራራ ድረስ ማንኛዪቱም ከተማ አላመለጠችንም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉን አሳልፎ በእጃችን ሰጠን።
እግዚአብሔርም፦ እርሱንና ሕዝቡን ሁሉ፥ ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአለሁና አትፍራው፤ በሐሴቦን ይኖር በነበረው በአሞሬዎናውያን ንጉሥ በሴዎን ላይ እንዳደረግህ በእርሱም ታደርግበታለህ አለኝ።
በሐሴቦንም ንጉሥ በሴዎን እንዳደረግን ፈጽሞ አጠፋናቸው፤ ከተሞቻቸውን ሁሉ በአንድነት፥ የሚሸሽ ሳናስቀር ሴቶችንም፥ ሕፃናቱንም ፈጽሞ አጠፋናቸው።
በሐሴቦን የተቀመጠው፥ በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም መካከል ጀምሮ የገለዓድን እኩሌታ እስከ ኢያቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፤
የአርሞንኤምን ተራራ፥ ካሴኪን፥ ባሳንንም ሁሉ እስከ ጌርጌሲና እስከ መከጢ ዳርቻ፥ የገለዓድንም እኩሌታ እስከ ሐሴቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ዳርቻ ድረስ የገዛው የባሳን ንጉሥ ዐግ፤
እንዲህም ሆነ፤ ከብዙ ዘመን በኋላ፥ እግዚአብሔርም እስራኤልን በዙሪያቸው ካሉት ጠላቶቻቸው ሁሉ ካሳረፈ በኋላ፥ ኢያሱ ሸመገለ፤ ዘመኑም ዐለፈ፤
በዚያም ጊዜ የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፤ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞሬዎናውያን ሀገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ ዐሥራ ስምንት ዓመት አስጨነቁአቸው።
አቤቱ ጠላቶችህ ሁሉ እንዲሁ ይጥፉ፤ ወዳጆችህ ግን ፀሐይ በኀይሉ በወጣ ጊዜ እንደሚሆን፤ እንዲሁ ይሁኑ። ምድሪቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረፈች።
ምድያምም በእስራኤል ልጆች ተዋረዱ፤ ራሳቸውንም ዳግመኛ አላነሡም፤ በጌዴዎንም ዕድሜ ምድሪቱ አርባ ዓመት ዐረፈች።