መሳፍንት 10:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 በዚያም ጊዜ የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፤ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞሬዎናውያን ሀገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ ዐሥራ ስምንት ዓመት አስጨነቁአቸው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 እነርሱም በዚያ ዓመት ሰበሯቸው፤ አደቀቋቸውም፤ ለዐሥራ ስምንት ዓመታት ከዮርዳኖስ ማዶ ባለው የአሞራውያን ምድር፣ በገለዓድ የነበሩትን እስራኤላውያንን ሁሉ አሠቃዩአቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 በዚያም ዓመት የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፥ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን አገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ ዐሥራ ስምንት ዓመት ተጋፉአቸው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 አሞናውያንና ፍልስጥኤማውያንም ከዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን ምድር በገለዓድ ውስጥ የሚኖሩትን እስራኤላውያንን ለዐሥራ ስምንት ዓመት አስጨንቀው ገዙአቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 በዚያም ዓመት የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፥ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን አገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ አሥራ ስምንት ዓመት ተጋፉአቸው። Ver Capítulo |