Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 3:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በሐ​ሴ​ቦ​ንም ንጉሥ በሴ​ዎን እን​ዳ​ደ​ረ​ግን ፈጽሞ አጠ​ፋ​ና​ቸው፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት፥ የሚ​ሸሽ ሳና​ስ​ቀር ሴቶ​ች​ንም፥ ሕፃ​ና​ቱ​ንም ፈጽሞ አጠ​ፋ​ና​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በእያንዳንዱ ከተማ ያሉትን ወንዶቹን፣ ሴቶቹንና ልጆቻቸውን ጭምር በማጥፋት፣ በሐሴቦን ንጉሥ በሴዎን ላይ እንዳደረግነው ሁሉ፣ እነዚህንም ፈጽመን ደመሰስናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በሐሴቦንም ንጉሥ በሴዎን እንዳደረግን ፈጽሞ ደመሰስናቸው፥ እያንዳንዱን ከተማ፥ ወንዶችን፥ ሴቶችና ሕፃናት ሁሉ አጠፋናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከሐሴቦን ንጉሥ ሲሖን በወሰድናቸው ከተሞች ላይ ባደረግነው ዐይነት እነዚህን ከተሞች ሁሉ ደመሰስን፤ ወንዶችንና ሴቶችን፥ ሕፃናትም ሳይቀሩ አጠፋን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በሐሴቦንም ንጉሥ በሴዎን እንዳደረግን ፈጽሞ አጠፋናቸው፤ ከተሞቹን ሁሉ ከወንዶችና ከሴቶች ከሕፃናቶችም ጋር አጠፋናቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 3:6
12 Referencias Cruzadas  

እስ​ራ​ኤ​ልም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ይህን ሕዝብ አሳ​ል​ፈህ በእ​ጃ​ችን ብት​ሰ​ጠን እር​ሱ​ንና ከተ​ሞ​ቹን ሕርም ብለን እና​ጠ​ፋ​ዋ​ለን” ብለው ስእ​ለት ተሳሉ።


በሐ​ሴ​ቦን ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረ​ውን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ንጉሥ ሴዎ​ንን፥ በአ​ስ​ጣ​ሮ​ትና በኤ​ድ​ራ​ይን ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረ​ው​ንም የባ​ሳ​ንን ንጉሥ ዐግን ከገ​ደ​ሉት በኋላ፥


ደግ​ሞም አለ፦ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ሂዱ፤ የአ​ር​ኖ​ን​ንም ሸለቆ ተሻ​ገሩ፤ እነሆ፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ውን የሐ​ሴ​ቦ​ንን ንጉሥ ሴዎ​ንን፥ ምድ​ሩ​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋን ግዛት፤ ውረ​ሳት፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ተዋጋ።


በዚ​ያን ጊዜም ከተ​ሞ​ቹን ሁሉ ወሰ​ድን፤ ከተ​ማ​ው​ንም ሁሉ፥ ሴቶ​ች​ንም፥ ሕፃ​ኖ​ች​ንም አጠ​ፋን፤ አን​ዳ​ችም የሸሸ በሕ​ይ​ወት አላ​ስ​ቀ​ረ​ንም፥


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ እዚህ ቦታ እስ​ክ​ት​ደ​ርሱ ድረስ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ች​ሁም፤ የወ​ይን ጠጅና የሚ​ያ​ሰ​ክ​ረ​ውን መጠ​ጥም አል​ጠ​ጣ​ች​ሁም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ እር​ሱ​ንና ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ ምድ​ሩ​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​አ​ለ​ሁና አት​ፍ​ራው፤ በሐ​ሴ​ቦን ይኖር በነ​በ​ረው በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ንጉሥ በሴ​ዎን ላይ እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ በእ​ር​ሱም ታደ​ር​ግ​በ​ታ​ለህ አለኝ።


እጅግ ብዙ ከሆ​ኑት ከፌ​ር​ዜ​ዎን ከተ​ሞች ሌላ፥ እነ​ዚህ ከተ​ሞች ሁሉ ቁመቱ ረዥም በሆነ ቅጥር በመ​ዝ​ጊ​ያና በመ​ወ​ር​ወ​ሪ​ያም የተ​መ​ሸጉ ነበሩ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የእ​ነ​ዚ​ህን ከተ​ሞች ምርኮ ሁሉ፥ ከብ​ቶ​ቹ​ንም ለራ​ሳ​ቸው ዘረፉ፤ ሰዎ​ቹን ሁሉ ግን እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በሰ​ይፍ ስለት መቱ​አ​ቸው፤ እስ​ት​ን​ፋስ ያለ​ው​ንም ሁሉ አን​ድም አላ​ስ​ቀ​ሩም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos