ትቶኛልና፥ ለሲዶናውያንም ርኵሰት ለአስጠራጢስ፥ ለሞአብም አምላክ ለኮሞስ፥ ለአሞንም ልጆች አምላክ ለሞሎክ ሰግዶአልና፥ አባቱም ዳዊት እንዳደረገ በፊቴ ቅን ነገርን ያደርግ ዘንድ በመንገዶቼ አልሄደምና።
መሳፍንት 10:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በዓሊምንና አስታሮትን፥ የሶርያንም አማልክት፥ የሲዶናንም አማልክት፥ የሞዓብንም አማልክት፥ የአሞንንም ልጆች አማልክት፥ የፍልስጥኤማውያንንም አማልክት አመለኩ፤ እግዚአብሔርንም ተዉ፤ አላመለኩትምም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን እንደ ገና በእግዚአብሔር ላይ ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ በኣልንና አስታሮትን እንዲሁም የአራምን፣ የሲዶናን፣ የሞዓብን፣ የአሞንንና የፍልስጥኤማውያንን አማልክት አመለኩ፤ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ስለ ተዉና ስላላገለገሉት፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላውያን እንደገና በጌታ ላይ ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ በኣልንና አስታሮትን እንዲሁም የሶሪያን፥ የሲዶናን፥ የሞዓብን፥ የአሞንንና የፍልስጥኤማውያንን አማልክት አመለኩ፤ እስራኤላውያን ጌታን ስለተዉና ስላላገለገሉት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ባዓልና ዐስታሮት የተባሉትን ባዕዳን አማልክት እንዲሁም የሶርያን፥ የሲዶናን፥ የሞአብን፥ የዐሞንንና የፍልስጥኤምን አማልክት በማምለክ እንደገና እግዚአብሔርን በደሉ፤ እርሱንም ማምለክ ተዉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ በኣሊምንና አስታሮትን የሶርያንም አማልክት፥ የሲዶናንም አማልክት፥ የሞዓብንም አማልክት፥ የአሞንንም ልጆች አማልክት፥ የፍልስጥኤማውያንንም አማልክት አመለኩ፥ እግዚአብሔርንም ተዉ፥ አላመለኩትምም። |
ትቶኛልና፥ ለሲዶናውያንም ርኵሰት ለአስጠራጢስ፥ ለሞአብም አምላክ ለኮሞስ፥ ለአሞንም ልጆች አምላክ ለሞሎክ ሰግዶአልና፥ አባቱም ዳዊት እንዳደረገ በፊቴ ቅን ነገርን ያደርግ ዘንድ በመንገዶቼ አልሄደምና።
ያንጊዜም ሰሎሞን ለሞአብ ርኵሰት ለኮሞስ፥ ለአሞን ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ በኢየሩሳሌም አንጻር በአለው ተራራ ላይ መስገጃን ሠራ።
በናባጥም ልጅ በኢዮርብዓም ኀጢአት መሄድ አልበቃውም፤ የሲዶናውያንንም ንጉሥ የኤያትባሔልን ልጅ ኤልዛቤልን አገባ፤ ሄዶም በዓልን አመለከ ሰገደለትም።
የአምላካቸውንም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ ተዉ፤ ቀልጠው የተሠሩትንም የሁለቱን እንቦሶች ምስሎች አደረጉ፤ የማምለኪያ ዐፀድንም ተከሉ፤ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ሰገዱ፤ በዓልንም አመለኩ።
በኢየሩሳሌምም ፊት ለፊት በርኵስት ተራራ ቀኝ የነበሩትን፥ የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ለሲዶናውያን ርኵስት ለአስታሮት፥ ለሞዓብም ርኵሰት ለካሞሽ፥ ለአሞንም ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ ያሠራቸውን መስገጃዎች ንጉሡ ርኩስ አደረገ።
ንጉሡም፥ “የመቱኝን የደማስቆን አማልክት እፈልጋቸዋለሁ፤ የሶርያን ንጉሥ እርሱን ረድተውታልና እኔንም ይረዱኝ ዘንድ እሠዋላቸዋለሁ” አለ። ነገር ግን ለእርሱና ለእስራኤል ሁሉ ዕንቅፋት ሆኑ።
ሲዶና ሆይ፥ ባሕር፥ የባሕር ምሽግ፥ “አላማጥሁም፥ አልወለድሁም፤ ጐበዛዝትንም አላሳደግሁም፥ ደናግልንም አላሳደግሁም” ብሎ ተናግሮአልና እፈሪ።
ሕዝቤ ሁለት ክፉ ነገሮችን አድርገዋልና፤ የሕይወት ውኃ ምንጭ እኔን ትተውኛል፥ የተነደሉትን ውኃውንም ይይዙ ዘንድ የማይችሉትን ጕድጓዶች ለራሳቸው ቈፍረዋል።
ከጥንት ጀምሬ ቀንበርሽን ሰብሬአለሁ፤ እስራትሽንም ቈርጫለሁ፤ አንቺም፦ አላገለግልም አልሽ፤ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ፤ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ተጋደምሽ።
እነርሱም ገብተው ወረሱአት፤ ነገር ግን ቃልህን አልሰሙም፤ በሕግህም አልሄዱም፤ ያደርጉም ዘንድ ካዘዝሃቸው ሁሉ ምንም አላደረጉም፤ ስለዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣህባቸው።
የሶርያም ሰዎች ከገንዘብሽ ብዛት የተነሣ ነጋዴዎችሽ ነበሩ፥ ከአንቺም ጋር አንድ ከሆኑ ከብዙ ሰዎች ጋር ትነግጂ ነበር፤ ነጭ ሐርንና ዕንቍን፥ ቀይ ሐርንና ወርቀ ዘቦን ከርከዴን የሚባል ዕንቍንና ልባንጃም የሚባል ሽቱን ከተርሴስ ያመጡልሽ ነበር፤ ገበያሽንም ረዓሙትና ቆርኮር መሉት።
“የአባትህ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብራህ የምትተኛ ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ ና፥ ሄደን አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢያስትህ፥
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ ከአባቶችህ ጋር ታንቀላፋለህ፤ ይህም ሕዝብ ይነሣል፤ ይቀመጥባትም ዘንድ በሚሄድባት ምድር መካከል ያሉትን ሌሎችን አማልክት ተከትሎ ያመነዝራል፤ እኔንም ይተወኛል፤ ከእነርሱም ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳሉ።
በዚያም ቀን ቍጣዬ ይነድድባቸዋል፤ እተዋቸውማለሁ፤ ፊቴንም ከእነርሱ እመልሳለሁ፤ ለጠላቶቻቸውም መብል ይሆናሉ፤ በዚያም ቀን፦ በእውነት አምላካችን እግዚአብሔር ትቶናልና፥ በእኛም መካከል የለምና ይህ ክፉ ነገር ሁሉ አገኘን እስኪሉ ድረስ ብዙ ክፉ ነገርና ጭንቀት ይደርስባቸዋል።
ያዕቆብ በላ፤ ጠገበም፤ የተወደደውን ጥጋብ አቀናጣው፤ ሰባ፥ ወፈረ፥ ሰፋ፤ የፈጠረውንም እግዚአሔርን ተወ፤ ከሕይወቱ ከእግዚአብሔርም ራቀ።
በባሳንም ያሉት የዐግ መንግሥት ከተሞች፥ አስጣሮትና ኤድራይን ነበረ። እነዚህም ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች ሆኑ፤ ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች እኩሌታም በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
አምላክህ ኮሞስ የሚሰጥህን የምትወርስ አይደለህምን? እኛም አምላካችን እግዚአብሔር ከፊታችን ያስወጣቸውን የእነርሱን ምድር የምንወርስ አይደለንምን?
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያን እጅ አርባ ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው።
የፍልስጥኤም መሳፍንትም፥ “አምላካችን ጠላታችንን ሶምሶንን በእጃችን አሳልፎ ሰጠን” እያሉ ለአምላካቸው ለዳጎን ታላቅ መሥዋዕት ይሠዉ ዘንድ፥ ደስም ይላቸው ዘንድ ተሰበሰቡ።
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረጉ፤ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረስተው በዓሊምንና አስታሮትን አመለኩ።
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግዚአብሔርም በምድያም እጅ ሰባት ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው።
እንዲህም ሆነ፤ ጌዴዎን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመለሱ፤ በዓሊምንም ተከትለው አመነዘሩ፤ በዓሊምም አምላክ ይሆናቸው ዘንድ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገቡ።