Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 23:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሲዶና ሆይ፥ ባሕር፥ የባ​ሕር ምሽግ፥ “አላ​ማ​ጥ​ሁም፥ አል​ወ​ለ​ድ​ሁም፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ት​ንም አላ​ሳ​ደ​ግ​ሁም፥ ደና​ግ​ል​ንም አላ​ሳ​ደ​ግ​ሁም” ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና እፈሪ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 አንቺ ሲዶና ሆይ፤ አንቺ የባሕር ምሽግ ሆይ፤ ዕፈሪ፤ ባሕሩ፣ “አላማጥሁም፤ አልወለድሁም፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን አላሳደግሁም” ብሏልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ባሕሩ “አላማጥሁም፤ አልወለድሁም፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን አላሳደግሁም” ብሏልና፥ አንቺ ሲዶና ሆይ፥ አንቺ የባሕር ምሽግ ሆይ፥ እፈሪ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የሲዶና ከተማ ሆይ! አንቺ በባሕር አጠገብ የተገነባሽ ጠንካራ ምሽግ ነሽ፤ ነገር ግን አንቺ ባል አግብታ ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወልዳ እንዳላሳደገች ሴት የተዋረድሽ ትሆኚአለሽ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4-5 ሲዶና ሆይ፥ ባሕር፥ የባሕር ምሽግ፦ አላማጥሁም፥ አልወለድሁም፥ ጎበዛዝትንም አላሳደግሁም፥ ደናግልንም አላሳደግሁም ብሎ ተናግሮአልና እፈሪ። ወሬዋ ወደ ግብጽ በደረሰ ጊዜ በጢሮስ ወሬ ምጥ ይይዛቸዋል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 23:4
12 Referencias Cruzadas  

የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፤ የሙሽራና የሙሽራይቱም ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፤ በአስማትሽም አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና።”


የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ወሰን ከሲ​ዶን እስከ ጌራ​ራና ጋዛ ድረስ ነው፤ ወደ ሰዶ​ምና ወደ ገሞራ፥ ወደ አዳ​ማና ወደ ሴባ​ዮም እስከ ላሳ ይደ​ር​ሳል።


ከነ​ዓ​ንም የበ​ኵር ልጁን ሲዶ​ንን፥ ኬጤ​ዎ​ንን፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ መቱ​አ​ቸ​ውም፤ ወደ ታላ​ቂ​ቱም ሲዶና፥ ወደ ማሴ​ሮ​ንም፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ወዳ​ለው ወደ ሞሳሕ ሸለቆ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ ማን​ንም ሳያ​ስ​ቀሩ መቱ​አ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በዓ​ሊ​ም​ንና አስ​ታ​ሮ​ትን፥ የሶ​ር​ያ​ንም አማ​ል​ክት፥ የሲ​ዶ​ና​ንም አማ​ል​ክት፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም አማ​ል​ክት፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች አማ​ል​ክት፥ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም አማ​ል​ክት አመ​ለኩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ተዉ፤ አላ​መ​ለ​ኩ​ት​ምም።


የጢ​ሮ​ስ​ንም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ፥ የሲ​ዶ​ና​ንም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ፥ በባ​ሕር ማዶ ያሉ የደ​ሴት ነገ​ሥ​ታ​ት​ንም፤


ወደ ይሁዳ ንጉ​ሥም ወደ ሴዴ​ቅ​ያስ፥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በመ​ጡት መል​እ​ክ​ተ​ኞች እጅ ወደ ኤዶ​ም​ያስ ንጉሥ፥ ወደ ሞዓ​ብም ንጉሥ፥ ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ፥ ወደ ጢሮ​ስም ንጉሥ፥ ወደ ሲዶ​ናም ንጉሥ ላክ።”


የሰው ልጅ ሆይ! ፊት​ህን ወደ ሲዶና አቅ​ን​ተህ ትን​ቢት ተና​ገ​ር​ባት፤ እን​ዲ​ህም በል፦


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሲዶና ሆይ! እነሆ በአ​ንቺ ላይ ነኝ፤ በው​ስ​ጥ​ሽም እከ​ብ​ራ​ለሁ፤ ፍር​ድ​ንም በአ​ደ​ረ​ግ​ሁ​ብሽ ጊዜ፥ በተ​ቀ​ደ​ስ​ሁ​ብ​ሽም ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቂ​ያ​ለሽ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios