አቤሴሎምንም ወስዶ በበረሓ ባለ በታላቅ ገደል ውስጥ ጣለው፤ እጅግም ታላቅ የሆነ የድንጋይ ክምር ከመረበት፤ እስራኤልም ሁሉ ሸሽተው ወደ ድንኳናቸው ገቡ።
ኢያሱ 7:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩ፤ እግዚአብሔርም ከቍጣው መቅሠፍት ተመለሰ። ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ዔሜቃኮር ተብሎ ተጠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአካንም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ የሚታየውን ታላቅ የድንጋይ ቍልል ከመሩበት፤ ከዚያም እግዚአብሔር ከአስፈሪ ቍጣው ተመለሰ። ስለዚህ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ያ ስፍራ የአኮር ሸለቆ ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሱም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩ፤ ጌታም ከጽኑ ቁጣው ተመለሰ። ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የአኮር ሸለቆ ተብሎ ተጠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርሱም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ የሚታይ ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት፤ እግዚአብሔርም ከቊጣው ተመለሰ፤ ስለዚህም ያ ቦታ የአኮር ሸለቆ ተብሎ ይጠራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩ፥ እግዚአብሔርም ከቁጣው ትኩሳት ተመለሰ። ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የአኮር ሸለቆ ተብሎ ተጠራ። |
አቤሴሎምንም ወስዶ በበረሓ ባለ በታላቅ ገደል ውስጥ ጣለው፤ እጅግም ታላቅ የሆነ የድንጋይ ክምር ከመረበት፤ እስራኤልም ሁሉ ሸሽተው ወደ ድንኳናቸው ገቡ።
የሳኦልን አጥንትና የልጁን የዮናታንን አጥንት፥ የተሰቀሉትንም ሰዎች አጥንት በብንያም በአባቱ በቂስ መቃብር አጠገብ ቀበሩአቸው፤ ንጉሡም ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ። ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ምድርን ሰማት።
አሁንም የቍጣውን መቅሠፍት ከእኛ እንዲመልስ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን አደርግ ዘንድ በልቤ አስቤአለሁ።
አለቆቻችንም በጉባኤው ፋንታ ሁሉ ይቁሙ፤ ስለዚህም ነገር የአምላካችን ጽኑ ቍጣ ከእኛ ይመለስ ዘንድ እንግዶቹን ሴቶች ያገቡት በከተሞቻችን ያሉት ሁሉ በተቀጠረው ጊዜ ይምጡ፤ ከእነርሱም ጋር የከተማው ሁሉ ሽማግሌዎችና ፈራጆች ይምጡ።”
ግብፃውያንስ፦ ‘በተራራ መካከል ሊገድላቸው፥ ከምድርም ፊት ሊያጠፋቸው ለክፋት አወጣቸው’ ብለው ስለ ምን ይናገራሉ? ከመዓትህ ተመለስ፤ ለሕዝብህም በክፋታቸው ላይ ራራ።
ካህናት ሆይ፥ ለኢየሩሳሌም ወደ ልቧ የሚገባ ነገርን ተናገሩ፤ ውርደቷ እንደ ተፈጸመ፥ ኀጢአቷም እንደ ተሰረየ፥ ከእግዚአብሔርም እጅ ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች አጽናኑአት።
ከዚያም የተገኘውን ገንዘብዋን እሰጣታለሁ፤ ምክርዋንም በአኮር ሸለቆ እገልጣለሁ፤ እንደ ሕፃንነትዋ ወራት፥ ከግብፅም እንደ ወጣችበት ቀን ትዘምራለች።
ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ፥ ቍጣው የዘገየ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።”
ያንም የእስራኤልን ሰው ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ። ሁለቱንም እስራኤላዊውን ሰውና ምድያማዊቱን ሴት ሆዳቸውን ወጋቸው፤ ከእስራኤልም ልጆች መቅሠፍቱ ተወገደ።
የእግዚአብሔር የመቅሠፍቱ ቍጣ ይመለስ ዘንድ፥ ለአባቶችህም እንደ ማለላቸው ይምርህ ዘንድ፥ ይራራልህም ዘንድ፥ ያበዛህም ዘንድ፥ ርጉም ከሆነው አንዳች ነገር በእጅህ አትንካ።
ዛሬም እኔ የማዝዝህን ትእዛዝ ሁሉ ብትጠብቅ፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ጥሩ የሆነውን ብታደርግ፥ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ ለእርሱ ልጅ ትሆናለህ።
ፀሐይም ልትገባ በቀረበች ጊዜ ኢያሱ አዘዘ፤ ከዛፎችም አወረዱአቸው፤ ተሸሽገውም በነበሩበት ዋሻ ጣሉአቸው፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዋሻው አፍ ታላላቅ ድንጋይ ተደርጎአል።
ኢያሱም የዛራን ልጅ አካንን፥ ብሩንም፥ ልብሱንም፥ ልሳነ ወርቁንም ወደ አኮር ሸለቆ ወሰዳቸው፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹንም፥ በሬዎቹንም፥ አህያዎቹንም፥ በጎቹንም፥ ድንኳኑንም፥ ንብረቱንም ሁሉ ወደ ዔሜቃኮር ወሰደ።
የጋይንም ንጉሥ በዝግባ ዛፍ ላይ ሰቀለው፤ እስከ ማታም ድረስ በዛፉ ላይ ቈየ። ፀሐይም በገባች ጊዜ ኢያሱ ያወርዱት ዘንድ አዘዘ፤ ከዛፉም አወረዱት፤ በከተማዪቱም በር አደባባይ ጣሉት፤ በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት።