Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሆሴዕ 2:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የበ​ዓ​ሊ​ምን ስሞች ከአ​ፍዋ አሰ​ወ​ግ​ዳ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፥ ስማ​ቸ​ውም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​ታ​ሰ​ብም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የበኣል አማልክትን ስም ከአንደበቷ አስወግዳለሁ፤ ከእንግዲህም ስሞቻቸው አይነሡም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ከዚያም የወይን ቦታዎችዋን፥ የተስፋ በርም እንዲሆናት የአኮርን ሸለቆ እሰጣታለሁ፤ በዚያም ከግብጽ ምድር እንደ ወጣችበት ቀን እንደ ብላቴንነትዋ ወራት ትዘምራለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ከአንደበትዋ የ“በዓል” ጣዖቶችን ስም ለማስወግድ የእነርሱ ስም ዳግመኛ አይጠራም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ከዚያም የወይን ቦታዋን፥ የተስፋ በርም እንዲሆንላት የአኮርን ሸለቆ እሰጣታለሁ፥ በዚያም ከግብጽ ምድር እንደ ወጣችበት ቀን እንደ ሕፃንነትዋ ወራት ትዘምራለች።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 2:17
8 Referencias Cruzadas  

የሰ​ውን ሥራ አፌ እን​ዳ​ይ​ና​ገር፥ ስለ ከን​ፈ​ሮ​ችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መን​ገ​ዶ​ችን ጠበ​ቅሁ።


በዚያ ጊዜም ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይህን መዝ​ሙር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘመሩ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ተና​ገሩ፦ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዘ​ም​ራ​ለን፤ በክ​ብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፤ ፈረ​ሱ​ንና ፈረ​ሰ​ኛ​ውን በባ​ሕር ጣለ።


ያል​ኋ​ች​ሁ​ንም ነገር ሁሉ ጠብቁ፤ የሌ​ሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት ስም አት​ጥሩ፤ ከአ​ፋ​ች​ሁም አይ​ሰማ።


እና​ን​ተም፦ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ያል​ፈ​ጠሩ እነ​ዚህ አማ​ል​ክት ከም​ድር ላይ፥ ከሰ​ማ​ይም በታች ፈጽ​መው ይጥፉ ትሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።


“ሂድ፤ እን​ዲህ ብለህ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጆሮ ተና​ገር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የብ​ላ​ቴ​ን​ነ​ት​ሽን ምሕ​ረት፥ የታ​ጨ​ሽ​በ​ት​ንም ፍቅር፥ በም​ድረ በዳ ዘር ባል​ተ​ዘ​ራ​በት ምድር እንደ ተከ​ተ​ል​ሽኝ አስ​ቤ​አ​ለሁ።


በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ የጣዖታትን ስም ከምድር አጠፋለሁ፥ ከዚያም በኋላ አይታሰቡም፣ ደግሞም ሐሰተኞችን ነቢያትና ርኩስ መንፈስን ከምድር ላይ አስወግዳለሁ።


በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል ወደ ቀሩት ወደ እነ​ዚህ አሕ​ዛብ አት​ግቡ፤ የአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ስሞች በእ​ና​ንተ መካ​ከል አይ​ጠሩ፤ አት​ማ​ሉ​ባ​ቸ​ውም፤ አታ​ም​ል​ኳ​ቸ​ውም፤ አት​ስ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤


በላ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ተመ​ለሰ። ስለ​ዚ​ህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ዔሜ​ቃ​ኮር ተብሎ ተጠራ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos