La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 21:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን ሴኬ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጌዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በተራራማው በኤፍሬም አገርም ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ሴኬምና ጌዝር፣

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነዚህንም ከተሞች ሰጡአቸው፤ በኤፍሬም ተራራማ አገር ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ሴኬምንና መሰማሪያዋን፥ ጌዝርንና መሰማሪያዋን፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለእነርሱም የተሰጡት አራት ከተሞች ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው ሴኬምና በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የሚገኙት የግጦሽ መሬቶችዋ፥ ጌዜር፥

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በኤፍሬም ተራራማ አገር ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ሴኬምንና መሰምርያዋን፥ ጌዝርንና መሰምርያዋን፥

Ver Capítulo



ኢያሱ 21:21
11 Referencias Cruzadas  

ድን​ኳ​ኑን ተክ​ሎ​በት የነ​በ​ረ​ው​ንም የእ​ርሻ ክፍል ከሴ​ኬም አባት ከኤ​ሞር ልጆች በመቶ በጎች ገዛው።


ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረገ፤ ከገ​ባ​ዖ​ንም እስከ ጌሴራ ድረስ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ።


እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ያነ​ግ​ሡት ዘንድ ወደ ሰቂማ መጥ​ተው ነበ​ርና ሮብ​ዓም ወደ ሰቂማ ሄደ።


በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ያሉ​ትን የመ​ማ​ፀ​ኛ​ውን ከተ​ሞች ሴኬ​ም​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፥ ደግ​ሞም ጋዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፤


በዚያ ጊዜም የጋ​ዜር ንጉሥ ኤላም ላኪ​ስን ለመ​ር​ዳት ወጣ፤ ኢያ​ሱም አንድ ስንኳ ሳይ​ቀር በሰ​ይፍ ስለት እር​ሱ​ንና ሕዝ​ቡን መታ፤ የዳ​ነም፥ ያመ​ለ​ጠም የለም።


በጋ​ዜ​ርም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን ኤፍ​ሬም አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በኤ​ፍ​ሬም መካ​ከል ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ገባ​ርም ሆኑ።


በን​ፍ​ታ​ሌም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር በገ​ሊላ ቃዴ​ስን፥ በኤ​ፍ​ሬ​ምም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ሴኬ​ምን፥ በይ​ሁ​ዳም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ኬብ​ሮን የም​ት​ባ​ለ​ውን የአ​ር​ቦ​ቅን ከተማ ለዩ።


ቄብ​ጻ​ይ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቤቶ​ሮ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው።


በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ሚካ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ።


የይ​ሩ​በ​ኣል ልጅ አቤ​ሜ​ሌ​ክም ወደ ሰቂማ ወደ እናቱ ወን​ድ​ሞች ሄደ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም፥ ለእ​ናቱ አባት ቤተ ሰቦ​ችም ሁሉ እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፦