Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 16:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በጋ​ዜ​ርም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን ኤፍ​ሬም አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በኤ​ፍ​ሬም መካ​ከል ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ገባ​ርም ሆኑ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ይህ ሁሉ ሆኖ የኤፍሬም ዘሮች በጌዝር የሚኖሩትን ከነዓናውያን ከዚያ አላባረሯቸውም ነበር፤ ከነዓናውያን እስከ ዛሬ ድረስ ከኤፍሬም ዘሮች ጋራ ዐብረው ይኖራሉ፤ ይሁን እንጂ የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ ይገደዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በጌዝርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላሳደዱአቸውም፥ እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ እነርሱም የጉልበት ሥራ የሚሠሩ ባሮች ሆነዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እነዚህ ኤፍሬማውያን ግን በጌዜር የሚኖሩ ከነዓናውያንን አላስወጡም ነበር፤ ስለዚህም ከነዓናውያን እስከ አሁን ድረስ በኤፍሬማውያን መካከል ይኖራሉ፤ ሆኖም ለኤፍሬማውያን የጒልበት ሥራ ለመሥራት ይገደዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በጌዝርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላሳደዱአቸውም፥ እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፥ የጉልበት ግብርም ያስገብሩአቸው ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 16:10
12 Referencias Cruzadas  

ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና ቤተ መን​ግ​ሥ​ቱን፥ ሜሎ​ን​ንም፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቅጥር፥ አሶ​ር​ንም፥ መጊ​ዶ​ንም፥ ጋዜ​ር​ንም ይሠራ ዘንድ ሠራ​ተ​ኞ​ችን መል​ምሎ ነበር።


የግ​ብ​ፅም ንጉሥ ፈር​ዖን ወጥቶ ጋዜ​ርን ያዘ፤ በእ​ሳ​ትም አቃ​ጠ​ላት፤ በሜ​ር​ጎብ ይኖሩ የነ​በ​ሩ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ላ​ቸው፤ ለል​ጁም ለሰ​ሎ​ሞን ሚስት እነ​ዚ​ያን አገ​ሮች ትሎት አድ​ርጎ ሰጥ​ቶ​አት ነበር።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ያጠ​ፉ​አ​ቸው ዘንድ ያል​ቻ​ሉ​ትን፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ሰሎ​ሞን እሰከ ዛሬ ድረስ ገባ​ሮች አድ​ርጎ መለ​መ​ላ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ያላ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውን፥ በኋ​ላ​ቸ​ውም በም​ድር ላይ የቀ​ሩ​ትን ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ሰሎ​ሞን እስከ ዛሬ ድረስ ገባ​ሮች አደ​ረ​ጋ​ቸው።


በዚያ ጊዜም የጋ​ዜር ንጉሥ ኤላም ላኪ​ስን ለመ​ር​ዳት ወጣ፤ ኢያ​ሱም አንድ ስንኳ ሳይ​ቀር በሰ​ይፍ ስለት እር​ሱ​ንና ሕዝ​ቡን መታ፤ የዳ​ነም፥ ያመ​ለ​ጠም የለም።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ግን የይ​ሁዳ ልጆች ሊያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ቸው አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም፤ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም እስከ ዛሬ ድረስ በይ​ሁዳ ልጆች መካ​ከል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ ተቀ​ም​ጠ​ዋል።


ይኸ​ውም በም​ናሴ ልጆች ርስት መካ​ከል ለኤ​ፍ​ሬም ልጆች ከተ​ለዩ ከተ​ሞች ጋር፥ ከተ​ሞች ሁሉ ከመ​ን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ጋር ነው።


የም​ናሴ ልጆ​ችም የእ​ነ​ዚ​ህን ከተ​ሞች ሰዎች ማጥ​ፋት ተሳ​ና​ቸው፤ ነገር ግን ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በዚ​ያች ሀገር ለመ​ቀ​መጥ መጡ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በረ​ቱ​ባ​ቸው፤ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም ገዙ​አ​ቸው፤ ነገር ግን ፈጽ​መው አላ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም።


ኤፍ​ሬ​ምም በጋ​ዜር የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው በጋ​ዜር ተቀ​መጡ፤ ገባ​ሮ​ችም ሆኑ​ላ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos