La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 2:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ፥ “ሀገ​ራ​ች​ንን ሁሉ ሊሰ​ልሉ መጥ​ተ​ዋ​ልና ወደ አንቺ የመ​ጡ​ትን በዚ​ችም ሌሊት ወደ ቤትሽ የገ​ቡ​ትን ሰዎች አውጪ በሉ​አት” ብሎ ወደ ረዓብ ላከ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የኢያሪኮም ንጉሥ፣ “ወደ አንቺ መጥተው ወደ ቤትሽ የገቡት ሰዎች ምድሪቱን በሙሉ ለመሰለል ስለ ሆነ፣ እንድታስወጪአቸው” የሚል መልእክት ወደ ረዓብ ላከ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የኢያሪኮም ንጉሥ እንዲህ ብሎ ወደ ረዓብ ላከ፦ “አገሩን ሁሉ ሊሰልሉ መጥተዋልና ወደ አንቺ የመጡትን ወደ ቤትሽም የገቡትን ሰዎች አውጪ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ የኢያሪኮ ንጉሥ “ምድሪቱን ሊሰልሉ የመጡ ስለ ሆኑ ወደ ቤትሽ የገቡትን ሰዎች አውጥተሽ አስረክቢ!” ብሎ ወደ ረዓብ ትእዛዝ ላከ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የኢያሪኮም ንጉሥ፦ አገሩን ሁሉ ሊሰልሉ መጥተዋልና ወደ አንቺ የመጡትን ወደ ቤትሽም የገቡትን ሰዎች አውጪ ብሎ ወደ ረዓብ ላከ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 2:3
15 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከሦ​ስት ወር በኋላ ለይ​ሁዳ፥ “ምራ​ትህ ትዕ​ማር ሴሰ​ነች፤ እነሆ፥ በዝ​ሙት ፀነ​ሰች” ብለው ነገ​ሩት። ይሁ​ዳም፥ “አው​ጡ​አ​ትና በእ​ሳት ትቃ​ጠል” አለ።


እኛም እን​ዲህ አል​ነው፥ “ሰላ​ማ​ው​ያን ሰዎች ነን እንጂ ሰላ​ዮች አይ​ደ​ለ​ንም፤


የአ​ሞ​ንም ልጆች አለ​ቆች ጌታ​ቸ​ውን ሐኖ​ንን፥ “ዳዊት አባ​ት​ህን በፊ​ትህ ለማ​ክ​በር አጽ​ና​ኞ​ችን ወደ አንተ የላከ ይመ​ስ​ል​ሃ​ልን? ዳዊ​ትስ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ለመ​መ​ር​መ​ርና ለመ​ሰ​ለል፥ ለመ​ፈ​ተ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን የላከ አይ​ደ​ለ​ምን?” አሉት።


የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮች ወደ ሴቲቱ ወደ ቤት መጥ​ተው፥ “አኪ​ማ​ሆ​ስና ዮና​ታን የት አሉ?” አሉ፤ ሴቲ​ቱም፥ “ፈፋ​ውን ተሻ​ግ​ረው ሄዱ፤ ጥቂ​ትም ቀደ​ሙ​አ​ችሁ” አለ​ቻ​ቸው። እነ​ር​ሱም ፈል​ገው አጡ​አ​ቸው፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተመ​ለሱ።


የአ​ሞን ልጆች አለ​ቆች ግን ሐና​ንን፥ “ዳዊት የሚ​ያ​ጽ​ና​ኑ​ህን ወደ አንተ የላከ አባ​ት​ህን በማ​ክ​በር ነውን? አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹስ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ለመ​መ​ር​መ​ርና ሀገ​ሪ​ቱ​ንም ለመ​ሰ​ለል ወደ አንተ የመጡ አይ​ደ​ሉ​ምን?” አሉት።


ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ክፉ ቀን ትጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለች፤ በቍጣ ቀንም ይወ​ስ​ዱ​ታል።


“ተሳ​ዳ​ቢ​ውን ከሰ​ፈር ወደ ውጭ አው​ጣው፤ የሰ​ሙ​ትም ሁሉ እጃ​ቸ​ውን በራሱ ላይ ይጫ​ኑ​በት፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት።”


ጲላ​ጦ​ስም እን​ደ​ገና ወደ ውጭ ወጣና፥ “እነሆ፥ በእ​ርሱ ላይ አን​ዲት በደል ስን​ኳን ያገ​ኘ​ሁ​በት እን​ደ​ሌለ ታውቁ ዘንድ ወደ ውጭ አወ​ጣ​ላ​ች​ኋ​ለሁ” አላ​ቸው።


ይዞም ወኅኒ ቤት አስ​ገ​ባው፤ ለሚ​ጠ​ብ​ቁት ለዐ​ሥራ ስድ​ስቱ ወታ​ደ​ሮ​ችም አሳ​ልፎ ሰጠው፤ ከፋ​ሲ​ካም በኋላ ወደ ሕዝብ ሊያ​ቀ​ር​በው ወድዶ ነበር።


ሄሮ​ድ​ስም ማለዳ ያቀ​ር​በው ዘንድ በወ​ደ​ደ​ባት በዚ​ያች ሌሊት ጴጥ​ሮስ ሁለ​ቱን እጆ​ቹን በሰ​ን​ሰ​ለት ታስሮ በሁ​ለት ወታ​ደ​ሮች መካ​ከል ተኝቶ ነበር፤ ጠባ​ቂ​ዎ​ችም የወ​ኅኒ ቤቱን በር ይጠ​ብቁ ነበር።


እን​ዲ​ህም አደ​ረጉ፤ አም​ስ​ቱ​ንም ነገ​ሥት፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ንጉሥ፥ የኬ​ብ​ሮ​ን​ንም ንጉሥ፥ የየ​ር​ሙ​ት​ንም ንጉሥ፥ የላ​ኪ​ስ​ንም ንጉሥ፥ የአ​ዶ​ላ​ም​ንም ንጉሥ ከዋ​ሻው ወደ እርሱ አወ​ጡ​አ​ቸው።


ለኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ፥ “እነሆ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሰላ​ዮች ሀገ​ራ​ች​ንን ሊሰ​ልሉ ወደ​ዚህ በሌ​ሊት ገቡ” ብለው ነገ​ሩት።


ሴቲ​ቱም ሁለ​ቱን ሰዎች ወስዳ ሸሸ​ገ​ቻ​ቸው፤ እር​ስ​ዋም፥ “አዎን፥ ሰዎቹ ወደ እኔ መጡ፤ ከወ​ዴት እንደ ሆኑ ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም፤


እር​ሱም፥ “ከድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ቁሚ፤ ሰውም መጥቶ፦ ‘በዚህ ሰው አለን?’ ብሎ ቢጠ​ይ​ቅሽ አንቺ፦ ‘የለም’ ትዪ​ዋ​ለሽ” አላት።